ስዊድን የመካከለኛው ምስራቅ፣ አፍሪካ እና ምስራቅ አውሮፓ ስደተኞችን በመቀበል ትታወቅ ነበር
ስዊድን በታሪክ ዝቅተኛ ስደተኛ ጠያቂዎች እንዳሏት ገለጸች።
ስዊድን በጦርነት እና አለመረጋጋት ምክንያት የሚፈናቀሉ ስደተኞችን በማስጠለል ትታወቃለች።
አውሮፓዊቷ ስዊድን በተለይን ጦርነት ርና መፈናቀል ከማይጠፋበት አፍሪካ የሚሰደዱ ስደተኞችን ስታስጠልል ቆይታለች።
ቀኝ አክራሪ ፓርቲዎች ወደ ስልጣን ከመጡ ጊዜ ጀምሮ ግን በስደተኞች ላይ ጥብቅ ህግን መከተል ጀምራለች።
ይህን ተከትሎም በተያዘው የፈረንጆቹ 2024 ዓመት ውስጥ በታሪክ ዝቅተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞችን ተቀብላለች።
የሀገሪቱ ስደተኞች ኤጀንሲ እንዳስታወቀው በ2024 ዓመት ወደ ስዊድን ከገቡ ስደተኞች ይልቅ ስዊድንን የለቀቁ ስደተኞች ቁጥር ይበልጣል።
የስደተኞች ኤጀንሲ ሚንስትር ማሪያ ማልመር እንዳሉት ከጥር እስከ ግንቦት ወር ድረስ ባሉት አምስት ወራት ውስጥ 5 ሺህ 700 ስደተኞች ስዊድንን ለቀው ወደ ሌሎች ሀገራት ተሰደዋል።
ከ2024 በፊት በነበሩት ዓመታት ውስጥ የአመልካች ስደተኞች ቁጥር በየዓመቱ በ15 በመቶ ሲቀንስ እንደነበር ተገልጿል።
በ2023 ዓመት ደግሞ በተለይም የኢራቅ፣ ሶማሊያ እና ሶሪያ የተወለዱ ዜጎች በስዊድን ለመኖር ያመለከቱ ሰዎች ቁጥር ጨምሮ ነበር ተብሏል።
ይሁንና በተያዘው ዓመት ደግሞ ከሶስቱ ሀገራት አንድም ስደተኛ ዜጋ የመኖሪያ ጥያቄ እንዳላቀረበ ተገልጿል።