ስዊድን 32ኛ አባል በመሆን ኔቶን ተቀላቀለች
ፊንላንድ ጥምረቱን የተቀላቀለችው ባለፈው አመት ሲሆን ቱርክ እና ሀንጋሪ ቶሎ ይሁንታ ባለመስጠታቸው ምክንያት የስዊድን ሊዘገይ ችሏል
ሰዊድን በአሜሪካ ዋሽንግተን በተካሄደ ስነስርአት ላይ ሰነድ በማስገባት 32ኛ አባል በመሆን ኔቶን ተቀላቅላለች
ሰዊድን በአሜሪካ ዋሽንግተን በተካሄደ ስነስርአት ላይ ሰነድ በማስገባት 32ኛ አባል በመሆን የምዕራባውያን ወታደራዊ ጥምረት የሆነውን ኔቶን ተቀላቅላለች።
የስዊድን ጠቅላይ ሚኒስትር ኡልፍ ክሪስተርሰን በዛሬው እለት ለአሜሪካ መንግስት ሰነድ በማሰረከብ ኔቶን ለመቀላቀል የሚያስፈልገውን የመጨረሻውን ሂደት መከወናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
"የታገሰ ጥሩ ነገር ያጋጥመዋል" ሲሉ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ስዊድን የተቀላቀለችበትን ሰነድ ሲቀበሉ ተናግረዋል።
ብሊንከን "ይህ ለስዊድን፣ ለጥምረታችን እና የትራንስአትላንቲክ ግንኙነት ታሪካዊ ክስተት"ብለዋል።
ከሩሲያ ጋር 1340 ኪሎሜትር የሚረዝም ድንበር ያላቸው ስዊድን እና ፊንላንድ ወደ ጥምረቱ መቀላቀል ለኔቶ ትልቅ ጠቀሜታ አለው ተብሏል። ይህ የጥምረቱን መዳከም ለሚፈልጉት ለሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ራስምታት ይሆንባቸዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ መክፈቷ ለበርካታ አስርት አመታት ከየትኛውም የዓለም ኃያል ጋር ባለመተባባር የሚታወቁትን የስካንዲኒቪያን ሀገራት የደህንነት ፖሊሲያቸውን እንዲቀይሩ አድርጓቸዋል።
በዚህ ምክንያት ሰዊድን እና ፊንላንድ ለደህንነታቸው ዋስትና ይሰጠናል ያሉትን በአሜሪካ የሚመራውን ኔቶን ተቀላቅለዋል።
ፊንላንድ ጥምረቱን የተቀላቀለችው ባለፈው አመት ሲሆን ቱርክ እና ሀንጋሪ ቶሎ ይሁንታ ባለመስጠታቸው ምክንያት የስዊድን ሊዘገይ ችሏል።
"ዛሬ ታሪካዊ ቀን ነው። ሰዊድን የኔቶ አባል ሆናለች" ያሉት የስዊድን ጠቅላይ ሚኒስትር ክሪስተርሰን ስዊድን ወደ ጥምረቱ መቀላቀሏ ከአጋሮቿ ጋር ሆና ደህንነቷን እንድታስጠብቅ ያስችላታል ብለዋል።