የእስር ቤቶች ዕጥረት የገጠማት ስዊድን የውጭ ሀገራት እስር ቤቶችን ልትከራይ ነው
በስዊድን የአደገኛ ወንጀል ፈጻሚ ቡድኖች ቁጥር እየጨመረ ነው ተብሏል
ሐገሪቱ አሁን ላይ ያሉኝ አልጋዎች 11 ሺህ ብቻ ነው ብላለች
የእስር ቤቶች ዕጥረት የገጠማት ስዊድን የውጭ ሀገራት እስር ቤቶችን ልትከራይ ነው።
አውሮፓዊቷ ስዊድን በአህጉሪቱ ከባድ ወንጀሎም በብዛት ከሚፈጸምባቸው ሀገራት መካከል ቀዳሚው ናት።
የወንጀል መጨመርን ተከትሎም ወደ እስር ቤት የሚገቡ ታሳሪዎች ቁጥር መጨመሩን ሮይተርስ ዘግቧል።
እንደ ዘገባው ከሆነ የወንጀለኞች መብዛት ሀገሪቱ ካሏት እስር ቤቶች ጋር ተመጣጣኝ ባለመሆኑ እስር ቤት ለመከራየት ማቀዷ ተገልጿል።
ስዊድን በፍርድ ቤት ጥፋተኝነታቸው የተረጋገጡ ወንጀለኞችን ወደ ሌሎች ሀገራት ለመላክ የተዘጋጀውን እቅድ ለማስፈጸም የሀገሪቱ ህግ አውጪ ምክር ቤት ማጽደቅ አለበት ተብሏል።
ሀገሪቱ እስረኞችን ወደ ውጭ ሀገራት ለመላክ ከማቀዷ ውጭ ወደ ይትኞቹ ሀገራት አዘዋውራ ልታስር እንደምትችል ግን አልጠቀሰችም።
አሁን ላይ ያለው የስዊድን ወንጀል መጠን ከ10 ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ እንደጨመረም ተገልጿል።
በ2023 የነበረው የወንጀል ምጣኔ ከ2024 ጋር ሲነጻጸር ደግሞ በ25 በመቶ ጭማሪ አሳይቷልም ተብሏል።
በስዊድን በተለይም በተቋማት እና ግለሰቦች ላይ የሚፈጸሙ ከባድ ወንጀሎች እየጨመረ ነው የተባለ ሲሆን ይህ መሆኑ ደግሞ የሚታሰሩ ሰዎችን ቁጥር እንዲጨምር አድርጓል።
በሀገሪቱ ሙዲና ስቶኮልም በተያዘው ጥር ወር ውስጥ ብቻ 30 የቦምብ ጥቃቶች እንደተፈጸሙም ተገልጿል።
አሁን እየተፈጸመ ያለው ወንጀል መጠን በዚሁ ከቀጠለ ስዊድን በ2033 27 ሺህ የእስር ቤት አልጋዎች ያስፈልጋታል ተብሏል።
ለዜጎች የተሻሉ እና ጥራት ያላቸው አገልግሎቶችን በመስጠት የምትታወቀው ስዊድን እስር ቤቶቿ ቅንጡ እና ደረጃቸውን የጠበቁ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል።