ስዊድናዊ ተመራማሪ ስቫንቴ ፓቦ የኖቤል ሽልማትን አሸነፉ
ተመራማሪው ሽልማቱን ያሸነፉት በሰው ልጅ አመጣጥ ሂደት ላይ በሰሩት ምርምር ነው
ስዊድናዊ ተመራማሪ አንድ ሚሊዮን ዶላር ገደማ ገንዘብ ይሸለማሉ
ስዊድናዊ ተመራማሪ ስቫንቴ ፓቦ የኖቤል ሽልማትን አሸነፉ።
በስዊድናዊ የድማሚት ቦምብ ፈጣሪ አልፍሬድ ኖቤል የተመሰረተው የኖቤል ሽልማት በየዓመቱ ይካሄዳል።
የዘንድሮውም ሽልማት በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት የቀጠለ ሲሆን በስነ ልቦና እና ህክምና ዘርፍ ስዊድናዊው ተመራማሪ ስቫንቴ ፓቦ አሸንፈዋል ሲል ተቋሙ አስታውቋል።
ተመራማሪው ሽልማቱን ያሸነፉት በሰው ልጅ አመጣጥ ሂደት ላይ በሰሩት ምርምር ነው ተብሏል።
በጀርመን ሙንሽ ዩንቨርስቲ እያስተማሩ የሚገኙት ፓቦ በሰው ልጅ አካል ውስጥ የሚገኙ ቅንጣቶች ላይ ምርምር ያደረጉ ሲሆን በተለይም ኒያንደርታል ስለሚባለው የሰው ዘር የዘረ መል ሂደትን በጊዜ ሂደት እስቀምጠዋል ተብሏል።
የተመራማሪው ግኝት ስለ ኒያንደርታል የሰው ዝርያ ከማሳወቁ ባለፈ በኮሮና ቫይረስ ወቅት የተለያዩ ህክምናዎችን ለማድረግ እድል እንደፈጠረም ተገልጿል።
የዘንድሮው የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊዎች ይፋ መደረግ የጀመሩ ሲሆን ዛሬ በህክምና ዘርፍ አሸናፊው ይፋ ሲደረግ በነገው ዕለት የፊዚክስ ከነገ በስቲያ ደግሞ የኬሚስትሪ በመቀጠል ደግሞ የስነ ጽሁፍ፣ ሰላም እና የኢኮኖሚ አሸናፊዎች ይፋ ይደረጋሉ ተብሏል።
የሰላም ኖቤል አሸናፊ 10 ሺህ የስዊድን ዲናር ወይም 920 ሺህ ዶላር ሽልማት ይበረከትለታል።
224 ሺህ ተመራማሪዎች በህክምና ዘርፍ የሰላም ኖቤል ሽልማትን የወሰዱ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሴት ሳይንቲስቶች ቁጥር 12 ብቻ ናቸው።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን በመጡበት በፈረንጆቹ 2018 ላይ የሰላም ኖቤል ሽልማት ማሸነፋቸው ይታወሳል።