
ስዊዘርላንድ በ2050 የነዳጅ አጠቃቀምን ለመቀነስ የሚያስችል እርምጃን ተራምዳለች
የስዊዘርላንድ መራጮች እሁድ እለት በንግድ ላይ የሚጣለውን ዝቅተኛ ግብርን ጨምሮ በ2050 የነዳጅ አጠቃቀምን ለመቀነስ እና ወደ ዜሮ ልቀት ለማድረስ የሚያስችል የአየር ንብረት ህግን አጽድቀዋል።
እሁድ በተደረገው ህዝበ ውሳኔ ከመረጡት ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት 11 በመቶ የነበረውን የሀገሪቱን የንግድ ግብር ምጣኔ 15 በመቶ እንዲሆን መርጠዋል።
ህጉ ሀገሪቱ ከውጭ ሀገር ድርጅቶች ምንም አይነት የገቢ ታክስ እንዳታጣ የሚያረጋግጥ ነው ተብሏል።
ጭማሪው ቢደረግም ስዊዘርላንድ አሁንም በዓለም ላይ ካሉት ዝቅተኛ የኮርፖሬት ታክስ ደረጃዎች ይኖራታል።
በሀገሪቱ ጎግልን ጨምሮ ሁለት ሽህ የሚሆኑ ግዙፍ የውጭ ድርጅቶች ይንቀሳቀሱ።
የአየር ንብረት ህጉም 59 በመቶ መራጮች ድጋፍ አግኝቷል።
ህጉ የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው የተባለ ሲሆን፤ እርምጃው ሀብታሟ ሀገር ማድረግ ያለባት ዝቅተኛው ነው ተብሏል።
ሆኖም የቀኝ ክንፍ ተቃዋሚዎች የኃይል ደህንነትን አደጋ ላይ ይጥላል ይላሉ።