ፖለቲከኛው ስም የማጠልሸት እርምጃ ነው ሲሉ የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ አድርገዋል
የሲሼልስ ፍ/ቤት የሀገሪቱን ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪና ሰባት ግለሰቦችን በመተት ጠርጥሮ መክሰሱ ተነግሯል።
ፓትሪክ ሄርሚኒ የተባሉት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ በ2025ቱ የሲሼልስ ምርጫ ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ውጥን ይዘዋል።
ፖለቲከኛው የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ አድርገዋል።
እስሩንና ክሱን የፖለቲካ እርምጃ ነው ያሉት ፓትሪክ ሄርሚኒ፤ የእሳቸውንና የፓርቲያቸውን ስም ለማጠልሸት የሚደረግ ጥረት ነው ሲሉ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኸን ተናግረዋል።
ፖሊስ ክሱ ከመቃብር ስፍራ ተቆፍረው ከወጡ ሁለት አስከሬኖች ጋር የሚያያዝ ነው ብሏል።
መገናኛ ብዙኸኑ እንደዘገቡት ፖለቲከኛውና ከእሳቸው ጋር የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ በርካታ ክሶች ቀርበውባቸዋል።
ከእነዚህ ክሶች ውስጥ ለጥንቁልና ይውላሉ የተባሉ ንጥረ-ነገሮችን መያዝና ለመጠንቆል በማሴር የሚሉ ክሶች ይገኙበታል።
ፖሊስ ፖለቲከኛው ከካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን ጨምሮ ከሌሎችም ተቋማት የተሰረቁ ሰነዶችን ይዘው መገኘታቸውን ገልጿል።
ከዚህም በተጨማሪም ፖሊስ በመስከረም ወር የጥንቁልና ግብዓቶችን ይዘው ተገኝተዋል ከተባሉ ተጠርጣሪዎች ጋር የስልክ ግንኙነት እንደነበራቸው አውቄአለሁ ብሏል።
ፓትሪክ ሄርሚኒና ሌሎች ስድስት ተጠርጣሪዎች በገንዘብ ዋስትና ተለቀዋል።ፖለቲከኛው ስም የማጠልሸት እርምጃ ነው ሲሉ የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ አድርገዋል