አህላም አልባሽር የተሰኘችው ይህች ሶሪያዊት ፈጽማዋለች በተባለ የሽብር ጥቃት 6 ሰዎች ሲገደሉ ከ100 በላይ ሰዎች ደግሞ እንደቆሰሉ ተገልጿል
የሽብርተኝት ወንጀል ፈጽማለች የተባለችው ተከሳሽ የ1 ሺህ 800 ዓመት እስር ተፈረደባት፡፡
የቱርክ ፍርድ ቤት ባስተላለፈው የፍርድ ትዕዛዝ የሽብር ወንጀል ፈጽማለች ያላትን አንድ ተከሳሽ በ1 ሺህ 800 ዓመት እስር እንድትቀጣ ወስኗል፡፡
እንደ ቱርክ ብዙሃን መገናኛዎች ዘገባ ከሆነ ተከሳሿ ከሁለት ዓመት በፊት በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ማዕከል በሆነችው ኢስታምቡል ልዩ ቦታው ኢስቲክላል በተሰኘ ስፍራ የተፈጸመውን የሽብር ትቃት አቀነባብራለች ተብሏል፡፡
በዚህ የሽብር ጥቃት ምክንያት ስድስት ሰዎች ሲገደሉ ከ100 በላይ ሰዎች ደግሞ የአካል ማጉደል አደጋ እንዳጋጠማቸው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
አህላም አልባሽር የተባለችው ይህች ተከሳሽ በዜግነት ሶሪያዊት ስትሆን በቱርክ ህግ አውጪ ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ፒኬኬ ቡድን አባል ነችም ተብሏል፡፡
ታዋቂው የቱርክ ተዋናይ ትምህርት ቤቱን ወደፍርስራሽነት ለውጦታል
ተከሳሿ ከዚህ የሽብር ቡድን ተልዕኮ በመቀበል በኢስታምቡል ህዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ በተፈጸመ የሽብር ጥቃት ዋነኛ ተዋናይ ነች በሚል በሰባት ወንጀሎች የእድሜ ዘመን እስር ተላልፎባታል፡፡
ተጠርጣሪዋ በተከሰሰችበት የተናጥል እና የቡድን ክሶች ላይ ድርጊቱን የፈጸመችው በፒኬኬ ቡድን ታዛ መሆኑን ለፍርድ ቤት መናገሯል ተገልጿል፡፡
በአጠቃላይ ይህች ሶሪያዊት ተከሳሽ በ1 ሺህ 800 ዓመት እስር እንድትቀጣ የተወሰባት ሲሆን በሌሎች ተባባሪ ተከሳሾችም ላይ ከእድሜ ልክ እስራት ጀምሮ የተለያዩ የቅጣት ውሳኔዎች ተላለፈዋል፡፡
የኢስታምቡል ፍርድ ቤትም በዚህ ወንጀል ከተከሰሱ 20 ተጠርጣሪዎች መካከል በአራቱ ላይ የእድሜ ልክ እስራት ውሳኔ ማስተላለፉ ተገልጿል፡፡