አሜሪካ በኢራን ይደገፋሉ ባለቻቸው ታጣቂዎች ላይ የአየር ላይ ጥቃት ማድረሷን አስታውቃለች
በሶሪያ ያሉ የአሜሪካ ወታደሮች በድሮን ጥቃት መጎዳታቸው ተገለጸ።
የአሜሪካ ወታደሮች እስላሚክ ስቴት የተሰኘውን የሽብር ቡድን ለመዋጋት በሚል ነበር ጦሯን ወደ ሶሪያ የላከችው።
የሶሪያ ፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ ተቃዋሚዎች በተቆጣጠሯቸው አካባቢዎች የሰፈረው የአሜሪካ ጦር የድሮን ጥቃት እንደደረሰበት ሮይተርስ ዘግቧል።
የአሜሪካ መከላከያ ሚንስትር ሊዮልድ ኦስቲን እንዳሉት በምስራቃዊ ሶሪያ ባለው የአሜሪካ ጦር ካምፕ ላይ የድሮን ጥቃት ደርሷል ብለዋል።
በኢራን አብዮተት ጠባቂ ወታደሮች ይደገፋል የተባለ ቡድን የድሮን ጥቃቱን እንዳደረሱ የተናገሩት ሚንስትሩ በጥቃቱም አንድ አሜሪካዊ ኮንትራክተር ሲገደል ስድስት የፔንታጎን ወታደሮች ደግሞ ቆስለዋል ተብሏል።
አሜሪካ የድሮን ጥቃት ሰንዝሯል በተባለው ቡድን ላይ የአየር ላይ ጥቃት ማድረሷን አስታውቃለች።
ይህ ቡድን ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ 78 ጊዜ በአሜሪካ ወታደሮች ላይ ጥቃት መሰንዘሩንም ሚንስትሩ አክለዋል።
ሶሪያ በግዛቷ ያለው የአሜሪካ ጦር ሀገሯን ለቆ እንዲወጣ በተደጋጋሚ የጠከቀች ሲሆን ዋሽንግተን በበኩሏ አይኤስ የሽብር ቡድን ዳግም ሊያንሰራራ እና ጥቃት ሊያዱርስ ይችላል የሚል ስጋቷን አስቀምጣለች።
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሶሪያ እና ኢራቅ ያለው የአሜሪካ ጦር በ2018 እንዲያበቃ ከወሰኑ በኋላ ውሳኔያቸው ዳግም መሻራቸውን ተከትሎ ጦሩ አሁንም በዛው ቀጥሏል።