የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ታባኔ ስልጣን መልቀቅ በሀገሪቱ ያለውን የፖለቲካ ቀውስ ያስወግዳል ተብሏል
የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ታባኔ ስልጣን መልቀቅ በሀገሪቱ ያለውን የፖለቲካ ቀውስ ያስወግዳል ተብሏል
የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶማስ ታባኔ በዛሬው እለት ስልጣን በመልቀቅ በተራራማዋ ደቡብ አፍሪካዊት ሀገር ከባለፈው አመት ጀምሮ በሀገሪቱ ሰፍኖ የነበረውን የፖለቲካ ቀውስ ያስወግዳል ተብሏል፡፡
ታባኔ የራሳቸው ፓርቲ “ኦል ባሶቶ ኮንቬንሽን”፣ተቃዋሚ ፓርቲዎችና የደቡብ አፍሪካ አስታራቂዎች፣ ታባኔና የአሁኗ ሚስታቸው ከሶስት አመት በፊት በቀድሞ ሚስታቸው ግድያ በመጠርጠራቸው ምክንያት ከስልጣን እንዲወርዱ ጫና ሲያሳድሩባቸው ቆይተዋል፡፡
ታባኔም ሆኑ አሁኗ ሚስታቸው በግድያው ላይ ተሳትፎ የለንም ብለው ክደዋል፡፡
“ትልቅ ቲያትር ከተሞላበት ድርጊትና ከህዝባዊ ህይወት እረፍት ማግኘት በመጨረሻም ደረስ“ በማለት የ80 አመቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ታባኔ በሌሴቶ ቴሌቪዝን መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ታባኔ ተተኪያቸው ለሆኑት ለአዲሱ ተመራጭ ህዝብ ድጋፍ እንዲሰጣቸው ተማጽነዋል፡፡
የፋይናንስ ሚኒስትር የሆኑት ሞይከትሲ ማጃሮ ታባኔን በመተካት ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል፡፡