የሼክ ታህኖን ቢን ዛይድ የአሜሪካ ጉብኝት በሀገራቱ መካከል እያደገ ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሚያጠናር ነው ተባለ
የአረብ ኢምሬትስ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪና የአቡዳቢ ም/አስተዳዳሪ ሼክ ታኖን ቢን ዛይድ በአሜሪካ ጉብኝ እያደረጉ ነው

የሼክ ታህኖን ቢን ዛይድ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስልጣን ከያዙ ወዲህ በአሜሪካ ጉብኝት ያደረጉ የመጀመሪያ ከፍተኛ የአረብ ኢምሬትስ ባለስልጣን ናቸው
የአረብ ኢምሬትስ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪና የአቡዳቢ ምክትል አስተዳዳሪ ሼክ ታኖን ቢን ዛይድ አል ናህያን የአሜሪካ ጉብኝት በሀገራቱ መካከል እያደገ ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሚያጠናር ነው ተባለ።
ሼክ ታኖን ቢን ዛይድ አል ናህያን በአሜሪካ የሚያደርጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በትናንትው እለት የጀመሩ ሲሆን፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስልጣን ከያዙ ወዲህ በአሜሪካ ጉብኝት ያደረጉ የመጀመሪያ ከፍተኛ የአረብ ኢምሬትስ ባለስልጣን ናቸው።
ጉብኝቱ ከ54 ዓመታት በፊት በጀመረው የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ታሪካዊ ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑም ተነግሯል።
ጉብኝቱ አረብ ኤሚሬትስ በዓለም ዙሪያ ካሉ ሀገራት ጋር የግንኙነት መስመሮችን ለማጠናከር፣ ውይይትን ለማስፋፋት እና ውጤታማ እና ሚዛናዊ አጋርነቶችን ለመፍጠር የምትከተለውን አካሄድ አካል ነው።
የሼክ ታህኖን ቢን ዛይድ በጉብኝታቸው ወቅት ምን ተግባራትን ይፈጽማሉ?
በጉብኝቱ ወቅት ሼክ ታህኑን ቢን ዛይድ አል ናህያን ከዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ የአስተዳደር ባለስልጣናት ጋር ይፋዊ ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ ተይዟል።
በዚሁ ወቅትም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊና ቴክኖሎጂያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ይደረጋል።
በተጨማሪም በአሜሪካ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መካከል ላለፉት አስርት ዓመታት የዘለቀውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሳደግ በሚቻልበት መንገዶች ላይ እንደሚወያዩም ይጠበቃል።
ጉብኝቱ በሀገራቱ መካከል እያደገ ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሚያጠናክር እንዲሁም እርስ በርስ በመደጋገፍ እና በሁለቱ ሀገራት ባለስልጣናት መካከል በሚደረጉ ውይይቶች ለማጠናከር የሚያዝ ነው ተብሏል።