ከቻይና ጋር ውጥረት ውስጥ የገባችው ታይዋን ለጦር ኃይሏ የምትመድበው አመታዊ በጀት በ14 በመቶ ለማሳደግ ማቀዷ አስታወቀች
ከፍተኛ ሪከርድ ያለው ይህ ፕሮፖዛል በደሴቲቱ በፓርላማ ይጸድቃል ተብሎም ይጠበቃል
ፕሬዝዳንት ጻይ ኢንግ ዌን የሀገሪቱ ጦር ኃይሎች ማዘመን ላይ ቅድሚያ ሰጥተው በመስራት ላይ መሆናቸው ይታወቃል
ከቻይና ጋር ውጥረት ውስጥ የገባችው ታይዋን ለጦር ኃይሏ የምትመድበው አመታዊ በጀት በ14 በመቶ ለማሳደግ ማቀዷ አስታወቀች፡፡
የሀገሪቱ ካቢኔ በዛሬው እለት ባካሄደው ስብሰባ ፤ እንደፈረንጆቹ 2023 ለታይዋን ጦር ኃይል የሚመደበው አመታዊ በጀት ወደ 13 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ ምክረ ሃሳብ መቅረቡ የሀገሪቱን ከፍተኛ ባለስልጣናት ነግረውኛል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ከታቀደው በጀት በተጨማሪ የታይዋን ፕሬዝዳንት ጻይ ኢንግ ዌን ካቢኔ ለተዋጊ ጄቶች እና ሌሎች መሳሪያዎች የሚውል ተጨማሪ የ108 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር በጀት ሀሳብ አቅርቧል።
ከፍተኛ ሪከርድ ያለው ይህ ፕሮፖዛል በደሴቲቱ በፓርላማ ይጸድቃል ተብሎም ይጠበቃል፡፡
ፕሬዝዳንት ጻይ ኢንግ ዌን የሀገሪቱ ጦር ኃይሎች ማዘመን ላይ ቅድሚያ ሰጥተው በመስራት ላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
የአሜሪካ አፈ ጉባኤ ናንሴ ፔሎሲ ቻይና የግዛቷ አካል አድርጋ የምታያትን ታይዋንን መጎብኘታቸውን ተከትሎ ቻይና በጣም ግዙፍ የተባለና ተከታታይ ወታደራዊ ልምምድ ማድረጓ ታይዋን ላይ ከፍተኛ ስጋት አሳድሯል፡፡
በዚህም ታይዋን ከቻይና ሊቃጣባት የሚችለውን ማንኛውም ጥቃት ለመከላከል ዝግጁ መሆኗ የታይዋን ፕሬዝደንት ጻይ ኢንግ ዌን በቅርቡ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡
የታይዋንዋ ፕሬዝዳንት የቻይና ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለታይዋን ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም ኃላፊነት የጎደለው ነውም ነበር ያሉት በወቅቱ፡፡
ፕሬዝዳንቷ “የሀገራችንን ሰላም እና መረጋጋት ለመጠበቅ እራሳችንን እንሰጣለን”ም ብለዋል፡፡