ታይዋን የቻይና የጦር መርከቦችና እና ጄቶች በታይዋን ዙሪያ ልምምድ እያደረጉ ነው ብላለች
ታይዋን ፤ ቻይና አሁንም በታይዋን ዙሪያ ወታደራዊ ልምምድ ማድረጋውን ቀጥለዋል አለች፡፡
የታይዋን መካላከያ ሚኒስቴር 17 የቻይና ተዋጊ ጄቶች እና አምስት መርከቦች በታይዋን ዙሪያ ተይዋል፤ የቻይና ወታደራዊ ልምምድም መቀጠሉን አስታውቋል፡፡
በልምምዱ ወቅት አራት የቻይና ጄቶች በሰላም ጊዜ እንደ ወሰን የሚያገለግለውን የታይዋን ስትሬት አማካኝ መስመር ማለፋቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የአሜሪካ አፈ ጉባኤ ናንሴ ፔሎሲ ቻይና የግዛቷ አካል አድርጋ የምታያትን ታይዋንን መጎብኘታቸውን ተከትሎ ቻይና በጣም ግዙፍ የተባለ ወታደራዊ ልምምድ አድርጋለች፡፡ ቻይና ወታደራዊ ልምምዱን ያደረገችው ለፔሎሲ ጉብኝት አጸፋ ሲሆን በአጭር ቀን ይቆማል የተባለው ልምምድ እስካሁን ቀጥሏል ስትል ታይዋን ድምጽ እያሰማች ነው፡፡
በፔሎሲ ጉብኝት ቻይና ክፉኛ ተቆጥታለች፡፡
ከፔሎሲ ጉብኝት በኋላም በአሜሪካ ህግ አውጭዎች የሚመራ የልኡክ ቡድን ታይዋንን ጎብኝቷል፡፡
ምንም እንኳን አሜሪካ ከታይዋን ጋር መደበኛ የሆነ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ባይኖራትም፣ ከታይዋን ጋር ያላት ግንኙነት የማጠናከር ፍላጎት አላት፡፡
አሜሪካ፣ ቻይና የግዛቷ አካል አድርጋ ከምታያት ታይዋን ጋር ያላትን ግንኙነት በቻይና ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ ቻይና በቅርቡ የአሜሪካ አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲን የታይዋን ጉብኝት ትንኮሳ ስትል ገለጸችው ሲሆን በፔሎሲ ላይ ማእቀብ መጣላ ይታወሳል፡፡
ቻይና በፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ምክንያት ከአሜሪካ ጋር የነበራትን ወታደራዊ ትብብር ማቋረጧን ማስታወቋ ይታወሳል፡፡