“እኛ አንተነኩስም፤ ነገርግን ራሳችንን እንከላከላለን”- የታይዋን ፕሬዝደንት
በፔሎሲ ጉብኝት የተቆጣችው ቻይና በታይዋን ዙሪያ ወታደራዊ ልምምድ እያደረገች ነው
በታይዋን ዙረያ ወታደራዊ ልምምድ እያደረገች ያለችው ቻይና ወደ ታይዋን ሚሳየል አስወንጭፋለች
የታይዋን ፕሬዝደንት ጻይ ኢንግ ዌን ሀገራቸው ማንንም እንደማትተነኩስና እና ነገርግን ራሷን እንደምትከላከል ተናግረዋል፡፡
የቻይና ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለታይዋን ብቻ ሳይሆን ለመላው አለም ኃላፊነት የጎደለው ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
“የሀገራችንን ሰላም እና መረጋጋት ለመጠበቅ እራሳችንን እንሰጣለን” ያሉት ፕሬዝዳንቷ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ፍትሃዊ ያልሆኑ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ለማስቆም እንዲተባበር ጠይቃለች።
እናም የታይዋን ፕሬዝዳንት በመቀጠል “የፀጥታው ሁኔታ እንዳይባባስ ከአጋሮቻችን ጋር እየተገናኘን ነው” ብለዋል።
ቻይና በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በእኛ ላይ የምታደርገውን የመረጃ ጦርነት አጠናክራ ስለምትቀጥል የታይዋን ህዝብ በንቃት እንዲጠብቅ አሳስባለች።
ፕሬዝደንት ጻይ ኢንግ ዌን "የፀጥታው ሁኔታ እንዳይባባስ ከአጋሮቻችን እየተነጋገርን ነው" ብለዋል፡፡
በአሜሪካዋ አፈጉባኤ ጉብኝት የታይዋን ጉብኝት የተበሳጨችው ቻይና በዛሬ እለት ጠዋት የባለስቲክ ሚሳየሎችን ወደ ታይዋን አስወንጭፋለች፡፡ የጃፓን መከላከያ ሚኒስትር አምስት የሚሆኑ የቻይና ሚሳየሎች በታይዋን ደሴት ላይ አልፈው በጃፓን በየኢኮኖሚ ዞን ማረፋቸውን ጠቅሷል፡፡
ሚኒስቴር በጃፓን ልዩ በሆነው የኢኮኖሚ ቀጠና ውስጥ የወደቁ ከሚመስሉት አምስት የቻይና ባሊስቲክ ሚሳኤሎች አራቱ “በዋናዋ የታይዋን ደሴት ላይ” መብረራቸው ጠቁሟል።
በፔሎሲ ጉብኝት የተቆጣችው ቻይና በታይዋን ዙሪያ ወታደራዊ ልምምድ እያደረገች ነው፡፡
አለምአቀፉ ማህበረሰብ የቻይናን ድርጊት እንዲያስቆም እየጠየቀች ያለችው ታይዋን፣ ቻይና ገፍታ ጦርነት የምትከፍት ከሆነ ግን ራሷን ለመከላከል እንደምትገደድ ገልጻለች፡፡