አስመራ፤ የአፈጉባኤዋ ጉዞ የአንድ ቻይና ፖሊሲን የሚቃነረን፤ የቻይናንም አንድነት የሚጻረረ ነው ብላች
ኤርትራ፤ የአሜሪካ ምክር ቤት አፈጉባዔ የታይዋን ጉብኝት ዓለም አቀፍ ህግን የጣሰ መሆኑን ገለጸች።
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፔሎሲን የታይዋን ጉብኝት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል። መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ ፖሊሲ የማይረባና በግልጽ የወጣ መሆኑን ጠቅሷል።
ዋሸንግተን ቻይናን ለመቆጣጠርና ለመያዝ ጥረት እያደረገች መሆኑን የገለጸችው አስመራ ይህ ድርጊት አጸያፊ ነው ብላለች።
ኤርትራ የፔሎሲ ጉብኝት ወደ ግጭት የሚያመራና የሚያባብስ እንደሆነም ነው የገለጸችው።
የአሜሪካ ምክር ቤት አፈጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ግደለሽነትን የሚያመለክት እንደሆነ ነው የገለጸችው።
አሜሪካ ባለፉት ዓመታት በእስያ የማሳመን ስራ ስትሰራ የቆየችው ይህንን ታይዋንን ጉዳይ ለማሳካት እንደሆነም ነው ኤርትራ ያስታወቀችው።
የአሜሪካ አፈጉባዔ ወደ ታይዋን ያደረጉት ጉዞ ከዓለም አቀፍ ህግና መርህ ያፈነገጠ ነውም ብሏል የኤርትራ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት።
የአፈጉባኤዋ ጉዞ ድርጊቱ ፤የቻይና መንግስት ሉዓላዊነት ደንቦችን እና ድንጋጌዎች እንዲሁም "የአንድ-ቻይና" ፖሊሲ የሚጻረር እና የቻይናውያን ውህደት ሂደትን የሚያደናቅፍ ነውም ብሏል የኤርትራ መንግስት።
ኤርትራ፤ የፔሎሲን የታይዋን ጉብኝት ያወገዘች ብቸኛ የአፍሪካ ሀገር ናት።
ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ ጉብኝቱን ማውገዛቸው ይታወሳል።