ቻይና ከአሜሪካ ጋር ያላትን ወታደራዊ ትብብርም ማቋረጧን ማስታወቋ ይታወሳል
የታይዋን መከላከያ ሚኒስቴር 17 የሚሆኑ የቻይና የጦር ጄቶች የባህር ክፍሏን ማቋረጣቸው እና በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበራዊ ድምበር መጣሳቸውን አስታውቋል፡፡
ታየዋን የቻይና የጦር ጄቶች በተደጋጋሚ በሁለቱ ሀገራት መካከል እንደ ድንበር የሚያገለገልውን ውሃ ወሰን ጥሰዋል በማለት ክስ ስታስማ ቆይታለች፡፡
የታይዋን መንግስት ቻይና አሁንም በታይዋን ዙሪያ የምታደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ መቀጠሏን ገልጻለች፡፡
ታይዋን በተመሳሳይ ከቻይና ሊሰነዘርባት ሚችለውን ጥቃት ለመመከት የሚያስችል ወታራዊ ልምምድ እደረገች መሆኑን መግለጿ ይታወሳል፡፡
የአሜሪከ አፈ-ጉባኤ ናንሴ ፔሎሲ ቻይና የግዛቷ አድርጋ የምትቆጥራትን ታይዋንን መጎብኘታቸውን ተከትሎ ቻይና አሜሪካ እና ታይዋን ጋር ያላት ግንኙነተ በከፍተኛ ደረጃ መሻከሩ የሚታወስ ነው፡፡
በፔሎሲ ግንኙነት የተቆጣችው ቻይና የአጸፋ እርምጃ የወሰደችው ታይዋንን በመክበብ ወታደራዊ ልምምድ በማድረግ ነበር፡፡ ከፔሎሲ ቀጥሎ ሌሎች ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣናት ታይዋንን የጎበኑ ሲሆን ቻይና ይህ እንቅስቃሴ የቻይና አንድ ቻይና ፖሊሲ የሚጻረረ ነው ሰትል በጽኑ ተቃውማለች፡፡
ቻይና ከአሜሪካ ጋር ያላትን ወታደራዊ ትብብርም ማቋረጧን ማስታወቋ ይታወሳል፡፡