ቻይና በታይዋን ዙሪያ ባደረገቸው ወታደራዊ ልምምድ 71 የጦር አውሮፕላኖችን ማሰማራቷ ተገለጸ
ቤጂንግ አሜሪካ ለታይዋን የምታደርገው ድጋፍ የቀጣነውን ውጥረት እንዳባባሰው ይገለጻል
ቻይና ወታደራዊ ልምምዱ ለአሜሪካ እና ታይዋን “ትንኮሳ” የተሰጠ ምላሽ ነው ብላለች
ቻይና በታይዋን ዙሪያ ባደረገቸው ወታደራዊ ልምምድ 71 የጦር አውሮፕላኖችን ማሰማራቷ የታይዋን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሕዝባዊ ነጻ አውጪ ጦር በመባል የሚታወቀው የቻይና ጦር በአሜሪካ እና በራስዋ በምትመራው ደሴት እየተስተዋለ ያለውን ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት በሚል እሁድ እለት “ወታደራዊ ልምምድ” ማድረጉን ገልጿል።
ከታይዋን የመከላከያ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው፤ ወታደራዊ ልምምዱ እስካሁን ይደረጉ ከነበሩት እጅግ ትልቅ የሚባል ነው፡፡
ሚኒስቴሩ በትዊተር ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ በልምምዱ 60 ተዋጊ ጄቶች የተሳተፉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የቻይና ዘመናዊ አውሮፕላኖች እንደሆኑ የሚነገርላቸው ስድስት ሱ-30 የጦር አውሮፕላኖች ናቸው ብሏል፡፡
ከዚህም በላይ 47ቱ በደሴቲቱ የአየር መከላከያ መለያ ዞን ውስጥ ተሻግረው መግባታቸውን የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ መረጃ ያመለክታል፡፡
ይሁን እንጅ በልምምዱ ጥቅም ላይ ውለዋል ስለተባሉት አውሮፕላኖች ብዛት በቤጂንግ በኩል የተባለ ነገር የለም፡፡
ታይዋን የምትኖረው ዲሞክራሲያዊት ደሴት የግዛቷ አካል እንደሆነች በምትናገረው በቻይና የማያቋርጥ የመወረር ስጋት ውስጥ መሆኑ ይታወቃል።
በፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ የምትመራው ቤጂንግ አሁን ላይ በታይዋን የምታደርገው ወታደራዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫናዋን ከፍ ማደርጓን ደግሞ የዚሁ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡
ሩስያ በዩክሬን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመመሯ ደግሞ ቻይና በታይዋን ላይ ተመሳሳይ ነገር ልትሞክር ትችላለች የሚል ስጋት እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል፡፡
አሜሪካ ለታይዋን የምትደርገው ድጋፍ ደግሞ ሌላው ቻይናን የቀጠናው ውጥረት እያባበሰ ያለ ጉዳይ እንደሆነ ይነሳል፡፡
በተለይም አሜሪካ ከቀናት በፊት ይፋ ያደገችው ታይዋንን ለመርዳት የሚያስችል አዲስ የመከላከያ ህግ ደግሞ ቤጂንግን እጅጉ ያስቆጣ እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡
ቤጂንግ የአሜሪካ ውሳኔ “በታይዋን የባህር ዳርቻ ሰላምና መረጋጋት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ ድንጋጌዎች” የያዘ ነው ስትል አዲሱን ህግ ማውገዟም አይዘነጋም፡፡