የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ከሩሲያ ጋር ግንኙነት ስለማጠናከር ያለን ውጥን ጠቆሙ
የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋንግ ዪ ቻይና ከሩሲያ ጋር "ስልታዊ የጋራ መተማመን እና የጋራ ተጠቃሚነት ትብብርን ታሰፋለች" ብለዋል
በሁለቱ የዓለም ታላላቅ የምጣኔ-ሀብት ባለቤቶች መካከል ላለው ግንኙነት መበላሸት አሜሪካ ተጠያቂ ተደርጋለች
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋንግ ዩ ቤጂንግ በመጪው ዓመት ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት እንደምታጠናክር አመልክተዋል።
ዋንግ በቻይና ዋና ከተማ በተካሄደው ጉባኤ ላይ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕት የዓለም ታላላቅ የምጣኔ-ሀብት ባለቤቶች በሆኑት አሜሪካ እና ቻይና መካከል ላለው የግንኙነት መበላሸት አሜሪካን ተጠያቂ አድርገዋል።
ቻይና “የአሜሪካን የተሳሳተ የቻይና ፖሊሲ በጥብቅ ውድቅ ታደርጋለች” ብለዋል።
ቻይና በምዕራቡ ዓለም በንግድ፣ በቴክኖሎጂ፣ በሰብዓዊ መብቶች እና በሰፊው የምዕራብ ፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ ያለውን የይገባኛል ጥያቄ በመቃወም አሜሪካን በጉልበተኝነት ወንጅላለች።
“የዩክሬንን ወረራ” ለማውገዝ እና በሩሲያ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ከሌሎች ሀገራት ጋር ለመቀላቀል ፈቃደኛ አለመሆኗ ከምዕራባዊያኑ ጋር ግንኙነቷን የበለጠ ያደናቀፈ እና ከአብዛኞቹ አውሮፓ ጋር መለያየት እንዲፈጠር አድርጓል ሲል አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።
ዋንግ እንዳሉት ቻይና ከሩሲያ ጋር "ስልታዊ የጋራ መተማመን እና የጋራ ተጠቃሚነት ትብብርን ታሰፋለች" ብለዋል።
"የዩክሬን ቀውስን በተመለከተ አንዱን ወገን ወይም ሌላውን ሳንደግፍ ወይም በእሳቱ ላይ ነዳጅ ሳንጨምር አሁንም ከሁኔታው ራስ ወዳድነትን ሳንፈልግ የግንዛቤ እና የገለልተኝነት መሰረታዊ መርሆችን እናከብራለን" ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ተናግረዋል።
ቻይናና ሩሲያ በምዕራቡ ዓለም ጫና ውስጥ በመሆናቸው በዚህም ከሞስኮ ጋር መግባባት ቢኖርም፤ የሀገሪቱ ምጣኔ-ሀብት ግን ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ገበያ እና ቴክኖሎጂ ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል።
ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ የቻይና ኢንዱስትሪ የበለጠ ራሱን እንዲችል እየገፋፉ ነው የተባለ ሲሆን፤ ነገር ግን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋንግ ከልምድ በመነሳት ቻይና እና አሜሪካ የአቅርቦት ሰንሰለቶችን ማጣመር ወይም መቆራረጥ እንደማይችሉ አምነዋል።
አሜሪካ ቻይናን እንደ ዋና ተፎካካሪዋ በመመልከቷ ቻይና ላይ ግልፅ የሆነ እገዳ ፣ ማፈን እና ማነሳሳት በመቀጠሏ የሻከረውን የሀገራቱን ግንኙነት ቤጂንግ ወደነበረበት ለመመለስ ትጥራለችም ብለዋል።