ልዩልዩ
“አደገኛው”ዲ.ኤፍ-100 የቻይና ክሩዝ ሚሳዔል
ሚሳዔሉ እስከ 3000 ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ የሚገኝ የጠላት ኢላማን ወደ አመድነት መቀየር አቅም አለው
ሚሳዔሉ ምድር ላይ እንዲሁም በውኃ ላይ የሚጓዙ የጦር መርከቦችን ማውደም ይችላል
ቻይና ካሏት “አገደኛ” የጦር መሳሪያዎች ውስጥ DF-100 ክሩዝ ሚሳዔል በቀዳሚነት ከሚነሱት ውስጥ ይገኛል።
ዲ.ኤፍ 100 ክሩዝ ሚሳዔል የመድር ለምድር ጥቃትን ለመፈጸም የሚውል ሲሆን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ጊዜ ይፋ የተደረገው ከሶስት ዓመት በፊት በፈረንጆቹ 2019 ነበር።
ይህ የሚሳዔል ስርዓት በመድር ላይ የሚገኙ የጠላት ኢላማዎችን ለማጥቃት እንዲቻል ተደርጎ ዲዛይን የተደረገ ሲሆን፣ በተጨማሪም ከምድር ስር ያሉ የጠላት ኢላማዎችን እንዲሁም በውሃ ላይ የሚጓዙ የጠላት የጦር መርከቦችን ማውደም የሚችል ነው።
ዲ.ኤፍ 100 ክሩዝ ሚሳዔል በአሁኑ ወቅት በቻይና ጦር ታጥቆት እየተጠቀመበት ያለ የጦር መሳሪያ መሆኑንም ይታወቃል።
አደገኛው ዲ.ኤፍ ክሩዝ ሚሳዔል ከ2 ሸህ እስከ 3 ሺክ ኪሎ ሜትር ርተት ውስጥ የሚገኝ የጠላት ኢላማን ወደ አመድነት የመቀየር አቅም እንዳለውም ነው የሚነገርለነት።
ሚሳዔሉ ትራንስፖርተር-ኤሬክተር-ላውነቸር (ቲ.ኢ.ኤል) በተባለ ግዙፍ ተሸከርካሪ የሚጓጓዝ ሲሆን፣ ተሸከርካሪው በአንድ ጊዜ ሁለት ዲ.ኤፍ 100 ሚሳዔሎችን መሸከም የሚችል ነው።