የናይጀሪያን ሰንደቅ አላማ የቀረጸው ሰው ህይወቱ ካለፈ አንድ ዓመት ቢሞላውም እስካሁን ስርዓተ ቀብሩ አልተፈተመም
ታይዎ አኪንኩንሚ ናይጀሪያ ከቅኝ ግዛት ነጻ ከወጣች በኋላ እየተጠቀመችበት ያለውን ሰንደቅ አላማ የቀረጸ ሰው ነበር
የአኪንኩንሚ ቤተሰቦች ለአስከሬኑ በቀን 2 ሺህ ኔይራ እየከፈሉ መሆኑን ተናግረዋል
የናይጀሪያን ሰንደቅ አላማ የቀረጸው ሰው ህይወቱ ካለፈ አንድ ዓመት ቢሞላውም እስካሁን ስርዓተ ቀብሩ አልተፈተመም
ታይዎ አኪንኩንሚ ናይጀሪያዊ ሲሆን ሀገሪቱ አሁን ላይ እየተጠቀመችበት ያለውን ሰንደቅ አላማ ቀለሞች የቀረጸ ሰው ሲሆን በመላው ሀገሪቱ የታወቀም ነው፡፡
ይህ ሰው በተወለደ በ87 ዓመቱ ከአንድ ዓመት በፊት ህይወቱ ያለፈ ሲሆን የሀገሪቱ መንግስት ተገቢውን ክብር በጠበቀ መልኩ በክብር ስርዓተ ቀብሩ እንደሚፈጸም አሳውቆ ነበር፡፡
ይህን ተከትሎም ቤተሰቦቹ የአኪንኩንሚን አስከሬን በቀን 2 ሺህ ኔይራ ወይም አንድ ዩሮ እየከፈሉ ካስቀመጡ አንድ ዓመት እንዳለፋቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡
የሟች ልጅ የሆነው አኪንዉሚ አኪንኩንሚ ለቢቢሲ እንዳለው የናይጀሪያ ባህል ሚኒስቴር ደውለውልኝ ለአባቱ መንግስታዊ የቀብር ስነ ስርዓት በኢባዳን ግዛት እንደሚካሄድ ከነገሩት በኋላ ድጋሚ የትኛውም አካል አነጋግረውት እንደማያውቁ ተናግሯል፡፡
የናይጀሪያ መንግስት ግን ታይዎ አኪንኩንሚ በዚህ ሳምንት በኦዮ ግዛት ክብሩን በጠበቀ መልኩ ስርዓተ ቀብሩ እንደሚፈጸም አስታውቋል፡፡
ታይዎ አኪንኩንሚ በ1960 በእንግሊዝ ትምህርት ላይ እያለ ናይጀሪያ አዲስ ሰንደቅ ዓላማ ለመቅረጽ ዓለም አቀፍ ጨረታ ማውጣቷን በጋዜጦች ለይ ካነበበ በኋላ ነበር የተወዳደረው፡፡
የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ሶስት ጀቶች በፈረንሳይ ታሰሩ
ናይጀሪያ በግብርና የታደለች ሀገር መሆኗን ለማሳየት አረንጓዴውን ቀለም እንዲሁም ነጩን ቀለም የናይጀሪያዊያንን አንድነት እና እኩልነት ለማንጸባረቅ በሚል እንዲሆን ለውድድር እንደላከውም አኪንኩንሚ በወቅቱ ተናግሮ ነበር፡፡
በወቅቱ ከመላው ዓለም ከሶስት ሺህ በላይ ተወዳዳሪዎች የሰንደቅ አላማ መወዳደሪያቸውን አስገብተው የነበረ ቢሆንም የአኪንኩንሚ አረንጓዴ እና ነጭ ቀለሞች ተወዳጅ ሆነው ተመርጠዋል፡፡
በናይጀሪያዊያን ዘንድ “የሰንደቅ ዓላማው ሰው” የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ሲሆን ሀገሪቱ ከብሪታንያ ቅኝ ግዛት ነጻ የወጣችበትን 50ኛ ዓመት ስታከብር ከምርጥ 50 የሀገሪቱ ዜጎች መካከል አንዱ ሆነው ብሔራዊ ጀግና ተብለው ተመርጠው ነበር፡፡