ቀሪ የኤምባሲ ሰራተኞችን ለማስወጣት ወደ አፍጋኒስታን የተላከው የአሜሪካ ጦር ካቡል ደረሰ
የታሊባን ጦር ካቡልን ለመቆጣጠር ተቃርቧል መባሉ የሚታወስ ነው
ጦሩ 3 ሺ የባህር ኃይል እና እግረኛ ጦር አባላትን አካቷል ተብሏል
አሜሪካ 3 ሺ የባህር ኃይል እና እግረኛ ጦር አባላትን ወደ አፍጋኒስታን መላኳ ተነገረ፡፡
የጦር አባላቱ ወደ አፍጋኒስታን የተላኩት የታሊባን ታጣቂዎች የአፍጋኒስታን ወሳኝ ከተሞችን እየተቆጣጠሩ ወደ ካቡል እየገሰገሱ መሆናቸውን ተከትሎ በካቡል ከተማ የቀሩ የአሜሪካ ኤምባሲ ሰራተኞችን ለማስወጣት ነው፡፡
3 ሺ አባላት ያሉት ሁለት ሻለቃ የባህር ኃይል እና አንድ ሻለቃ እግረኛ ጦር ወደ አፍጋኒስታን መላኩን የአሜሪካ መከላከያ መስሪያ ቤት (ፔንታጎን) አስታውቋል፡፡
ሮይተርስ አንድ ሰማቸው እንዲጠቀስ ያፈለጉ አሜሪካ ባለስልጣን ነገሩኝ ብሎ እንደዘገበው ትናንት ጭምር ካቡል የደረሱት ወታደሮቹ እስከ ነገ እሁድ ተጠቃለው ካቡል እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡
ፔንታጎን አንድ የውጊያ እግረኛ ቡድን አስፈላጊ ከሆነ በካቡል ውስጥ ለደህንነት ፈጣን ምላሽ ሰጭ ለመሆን ከሰሜን ካሮላይና ወደ ኩዌት ሊሄድ እንደሚችልም ጠቁሟል።
ታሊባን ወደ ካቡል እየገሰገሰ መሆኑን ተከትሎ የአፍጋኒስታን መንግስት ኃይሎች ከውድቀት ለመታደግ እንግሊዝ እንዲሁም ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ወታደሮቻቸውን ወደ ካቡል በመላክ ላይ ናቸው፡፡
የታሊባን ታጣቂዎች ወታደራዊ እርምጃና ፍጥነት የአፍጋን መዲና ካቡል ነዋሪዎችን እጅጉ እንዳስጨነቀ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
እስካሁን ባለው መረጃ በታጣቂዎቹ እና በመንግስት ባለው ግጭት በሺዎች የሚዎጠሩ የሀገሪቱ ዜጎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተፈናቅለዋል።
በአፍጋኒስታን ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ ያለው የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር (ኔቶ) እና የአሜሪካ ጦር ከ20 ዓመታት በኋላ መውጣታቸውን ተከትሎ እንደሆነ ሲገለጽ ቆይቷል።
ታሊባን የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋኒ ከስልጣን ካልተነሱ ሰላም እንደማይረጋገጥ ቀደም ብሎ መግለጹ ይታወሳል።
የአሜሪካ እና የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ከአፍጋኒስታን ለቆ መውጣት ከጀመረበት ዕለት ጀምሮ ታሊባን የአፍጋኒስታንን በርካታ ግዛቶች መቆጣጠሩን እየገለጸ ነው።
ታሊባን አስረኛዋ የአፍጋኒስታን ግዛት የሆነችውን እና ከ ካቡል 150 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ጋዝኒ ከተማ ከአንድ ቀን በፊት መቆጣጠሩ ይታወቃል፡፡