ታሊባን ወደ ስልጣን የተመለሰበትን 2ኛ አመት አከበረ
በሀገሪቱ የነበሩ የአሜሪካ ወታደሮች መውጣታቸውን ተከትሎ ከባድ ማጥቃት ያደረሰው ታሊባን ከ20 አመታት የማያባራ ጦርነት በኋላ በፈረንጆቹ ነሀሴ 2021 ካቡልን መግባት ቻለ
በአሜሪካ የሚደገፈው የአፍጋን ፕሬዝደንት አሽራፍ ጋኒ ሀገር ጥለው ሲሰደዱ በምዕራባውን ድጋፍ የተቋቋመዎ የአፍጋኒስታን ጦርም ተበታተነ
የአፍጋኒስታኑ ታሊባን ወደ ስልጣን የተመለሰበትን፣ ካቡልን የተቆጣጠረበትን እና እስላማዊ ስርአት የመሰረተበትኖ ሁለተኛ አመት አክብረዋል።
በሀገሪቱ የነበሩ የአሜሪካ ወታደሮች መውጣታቸውን ተከትሎ ከባድ ማጥቃት ያደረሰው ታሊባን ከ20 አመታት የማያባራ ጦርነት በኋላ በፈረንጆቹ ነሀሴ 2021 ካቡል መግባት ቻለ።
በአሜሪካ የሚደገፈው የአፍጋን ፕሬዝደንት አሽራፍ ጋኒ ሀገር ጥለው ሲሰደዱ በምዕራባውያን ድጋፍ የተቋቋመው የአፍጋኒስታን ጦርም ተበታተነ።
"ካቡልን የተቆጣጠርንበትን ሁለተኛ አመት ስናከብር ለዚህ ታላቅ ድል ያበቁንን ተዋጊዎች እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ" ሲሉ የታሊባን ቃል አቀባይ ዛቢሁላህ ሙጃሂድ ባወጡት መግለጫ ተናግረዋል።
ቀኑ ብሔራዊ በዓል እንዲሆን የታወጀ ሲሆን የጸጥታ ሀይሎች ፍተሻዎችን ማካሄዳቸውም ተዘግቧል።
በዓሉ በሚከበርበት ቦታ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ታድሟል። " አሁን የሀገሪቱ ደህንነት በሚገባ ተጠብቋል፤ የሀገሪቱ መላ ግዛት በአንድ አመራር እየተጠበቀ መሆኑን እና በሸሪኣ የሚመራ እስላማዊ ስርአት መዘርጋቱን" ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።
አፍጋኒስታን በአስርት አመታት ውስጥ ያልታየ ሰላም እያጣጣመች ቢሆንም ተመድ ንጹሃን ላይ ጥቃት እየደረሰ ነው የሚል ክስ እያቀረበ ነው።
በምዕራባውያን በሚደገፈው መንግስት ዘመን ሴቶች በርካታ መብቶች የነበሯቸው ሲሆን ታሊባን ከተመለሰ በኋላ ሴቶች ለመብት ረገጣ ሰለባ ሆነዋል።
ታሊባን በሴቶች ላይ የሚያራምደው ፖሊሲ ምዕራባውያን ለታሊባን እውቅና ለመስጠት ከሚቸገሩባቸው ምክንያቶች አንዱ ነው።