አፍጋኒስታንን እያስተዳደረ ያለው ታሊባን ከሴቶች ጋር የተያያዙ ክልከላዎችን በመደንገግ ላይ ይገኛል
ታሊባን የልብስ መሸጫ አሻንጉሊቶች ፊታቸው እንዲሸፈኑ አዘዘ።
ከሁለት ዓመት በፊት በትጥቅ ትግል አፍጋኒስታንን የተቆጣጠረው ታሊባን በየጊዜው የሴቶችን እንቅስቃሴ እና መብቶች የሚገድቡ ህጎችን እያወጣ ይገኛል።
አሁን ደግሞ የአልባሳት ነጋዴዎች ናሙናዎቻቸውን ለሸማቾች የሚያሳዩባቸውን የፕላስቲክ አሻንጉሊት ፊታቸውን እንዲሸፍኑ የሚያስገድድ ህግ ማውጣቱን ሮይተርስ ዘግቧል።
በልብስ ንግድ የተሰማሩ አፍጋናዊያን በበኩላቸው ታሊባን ህጉን እንዲያነሳላቸው በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ።
ከዚህ በፊት ታሊባን ሴቶች ወደ ዩንቨርስቲ እንዳይገቡ፣ መቀጠር እንዳይችሉ እና ካለ ወንድ ረጅም ርቀት መንገድ እንዳይጓዙ የሚከለክል ህግ ማውጣቱ ይታወሳል።
በሰብዓዊ መብት አያያዝ ከተመድ እና ከምዕራባዊያን ሀገራት ትችቶችን እያስተናገደ ያለው ታሊባን መራሹ የአፍጋኒስታን መንግሥት በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ አልሰጠም።
ታሊባን በአሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ጦር ይደገፍ የነበረውን የቀድሞ የአፍጋኒስታን መንግስትን በትጥቅ ትግል ከስልጣን ካስወገደ ሁለት ዓመት ሆኖታል።
አሜሪካ እና ምዕራባዊያን ሀገራትም የጦር መሳሪያቸውን ጥለው በአየር ከአፍጋኒስታን መውጣታቸውም አይዘነጋም።