አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ መክፈቻ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው
አምባሳደር ታዬ በአሁኑ ወቅት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት በመሆን በማገልገል ላይ ነበሩ
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡
ሁለቱ ምር ቤቶች በጋራ ባካሄዱት የመክፈቻ ስነ ስርዓትም አምባሳደር ታዬ አስጸቀስላሴ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟል።
የፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የሥራ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል።
አምባሳደር ፕሬዚዳንት ታዬም በምክር ቤቶቹ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡
ከቀድሞዋ ፕሬዚዳንት ሣለወርቅ ዘውዴም ሥራ እርክክብ አድርገዋል፡፡
አምባሳደር ታዬ፤ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ መምሪያ የሥራ ክፍል ፣የምዕራብ አውሮፓ ዋና ክፍል ኃላፊ፣የኢንፎርሜሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር፣ስቶክሆልም የኢፌዲሪ ኤምባሲ በአማካሪነት፣በዋሽንግተን የኢፌዲሪ ኤምባሲ በአማካሪነት።
በሎስአንጀለስ ቆንስል ጀነራል፣ በ1998ዓ.ም ባለሙሉሥልጣን አምባሳደርነት ተሹመዋል፣
በሎስአንጀለስ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት ማዕረግ የቆንስላ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ በአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል፣ በ2008 ዓ.ም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሰርተዋል።
በግብፅ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ተጠሪ ሆነው አገልግለዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ሰርተዋል፤አምባሳደር ታዬ በአሁኑ ወቅት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት በማገልገል ላይ እንደነበሩ ይታወቃል።