ቴዲ አፍሮ አዲስ ነጠላ ዜማ በነገው እለት እንደሚለቅ አስታወቀ
ከ20 ዓመት በፊት ነበር አቡጊዳ የተሰኘውን የመጀመሪያ አልበሙን ለአደማጭ ያደረሰው
አዲሱ ነጠላ ዜማ “አርማሽ ወይም ቀና በል” የሚል መጠሪያ እንዳለው አርቲስት አስታውቋል
ታዋቂው አርቲስት ቴዮድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ እንዳስታወቀው "አርማሽ ( ቀና በል)" የተሰኘ አዲስ ነጠላ ዜማ ነገ ዕረቡ ጥቅምት 24 ቀን 2014 ዓ.ም ይለቀቃል።
ነጠላ ዜማው በራሱ ቴዲ አፍሮ የዩቲዩብ ቻናል እንደሚለቀቅም ተገልጿል፡፡
የ45 ዓመቱ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ከ20 ዓመት በፊት ነበር አቡጊዳ የተሰኘውን የመጀመሪያ አልበሙን ለአደማጭ አድርሶ፤ ከፍተኛ አድናቆት ማግኘት ችሎ ነበር፡፡
አምስት አልበሞችን ለአድማጮች ያደረሰው ቴዲ አፍሮ ከሰባት በላይ ተወዳጅ ነጠላ ዜማዎችን ለአድማጮቹ አቅርቧል፡፡
ጎንደር ዩንቨርሲቲ ከሁለት ወራት በፊት ለቴዲ አፍሮ የክብር ዶክትሬት ድግሪ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ ዩኒቨርሲቲው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በሰብዓዊ፣ በማኅበራዊና በኪነ ጥበብ ዘርፉ እያበረከተ ላለው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነው የክብር ዶክተሬቱን እንተበረከተለት ዩኒቨርሲተው ማስታወቁ ይታወሳል፡፡