የቴሌግራም መስራች ዱሮቭ ከ100 በላይ ልጆች እንዳሉት ማወቁን ገለጸ
ትውልደ ሩሲያዊ የሆነው የቴሌግራም ባለቤት እና መስራች ፓቬል ዱሮቭ በቅርቡ በቴሌግራም ገጹ የሚገርም መረጃ ይፋ አድርጓል
ይህ መረጃ ያላገባው እና የብቸኝነት ህይወት የመረጠው የቴክኖሎጂ ቢሊየነር የግል ህይወት ትኩረትን ስቧል።
የቴሌግራም መስራች ዱሮቭ ከ100 በላይ ልጆች እንዳሉት ማወቁን ገለጸ።
ትውልደ ሩሲያዊው የሆነው የቴሌግራም ባለቤት እና መስራች ፓቬል ዱሮቭ በቅርቡ በቴሌግራም ገጹ የሚገርም መረጃ ይፋ አድርጓል።
ዱሮቭ በቪትሮ ፈርቲላይዜሽን(አይቪኤፍ) አማካኝነት ከ100 በላይ ለሚሆኑ ልጆች ከባት መሆኑን ገልጿል።
ይህ መረጃ ያላገባው እና የብቸኝነት ህይወት የመረጠው የቴክኖሎጂ ቢሊየነር የግል ህይወት ትኩረትን ስቧል።
ዱሮብ እንዳብራራው ከ15 አመታት በፊት ለመጸነስ ተቸግራ የነበረችውን ጓደኛውን ለመርዳት አርቴፊሻል በሆነ መንገድ ለሚያራባ ክሊኒክ ስፐርም( የወንድ ዘር ፈሳሽ) ሰጥቷል። ዱሮብ ይህን ስጦታውን ለመጸነስ የፈለገችን ጓደኛ የመርዳት በጎ ተግባር አድርጎ እንደወሰደው ይገልጻል።
ይህ የደግነት ስራው ያልተጠበቀ ነገር እንደሚያስከትል አያውቅም ነበር።
ዱሮብ እንደገለጸው ስፐርም የለገሰበት ክሊኒክ መጸነስ ለሚፈልጉ ቤተሰቦች ሁሉ ሲጠቀም ቆይቷል። የእሱ ስፐርም ከ100 ጊዜ በላይ ጥቅም ላይ ውሎ በተለያየ አለም ያሉ ሴቶች እንዲወልድ አድርጓል። ይህ ያልተጠበቀ ግኝት የብቸኝነት ህይወት የሚመርጠውን ዱሮቭ አስደንግጧል።
ይህ ዜና በስፋት የሚዲያ ትኩረትን የሳበ ሲሆን ከሰው ተገልሎ በብቸኝነት በመኖር የሚታወቀውን ድሮብ ባልጠበቀው ሁኔታ መነጋገሪያ እንዲሆን አድርጎታል።
ዱሮብ በፈረንጆቹ 2013 ያበለጸገው የመልእክት መለዋወጫው ቴሌግራም ተጠቂሚዎች ቁጥር በአሁኑ ወቅት ወደ አንድ ቢሊዮን እየደረሰ ነው። ለቴሌግራም ተጠቃሚዎች ቁጥር በፍጥነት ማደግ እየተስፋፉ ያሉት የክሪፕቶ ጌሞች አስተዋጽኦ አላቸው።