በአስር ሺህ የሚቆጥሩ ሱዳናዊያንን ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል
ሰልፈኞቹ የሉአላዊ የሽግግር ም/ቤት መሪ ጀነራል አል ቡርሀን ስልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል
በአስር ሺህ የሚቆጥሩ ሱዳናዊያንን በካርቱም ወታደራዊ አመራሩን ተቃውመው አደባባይ ወጥተዋል
በአስር ሺህ የሚቆጥሩ ሱዳናዊያን በሀገሪቱ መዲና ካርቱም በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ (ዶ/ር) ለሚመራው የሱዳን የሲቪል አስተዳድር ድጋፍ ለመስጠት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል፡፡
ሰልፈኞቹ የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል አልቡርሀን ስልጣን እንዲለቅ ጠይቀዋል፡፡ሰልፈኞቹ“አብዮት መብታችን ነው፤ ፍትህ እና ሰላም እንፈልጋለን” የሚል መፈክር አስምተዋል፡፡
- የሱዳን መፈንቅለ መንግስት ሙከራን ተከትሎ የሲቪልና ወታደራዊ አመራሮች እየተካሰሱ ነው
- የአልበሽር ለአይ.ሲ.ሲ ተላልፎ መሰጠት ጉዳይ “በሱዳን ካቢኔ አባላት መካከል መከፋፈልን ፈጥሯል” ተባለ
የሀገሪቱ ጦረም በካርቱም ዋና ዋና አደባባዮች ላይ ጥበቃ በማድረግ ላይ ሲሆን የመገበያያ ቦታዎች እና ሱቆች በሰልፉ ምክንያት ተዘግተዋል ተብሏል፡፡
የሰልፉ አስተባባሪ አሊ አማር በሲቪል አስተዳድር የሚመራ መንግስት እንዲኖረን ሱዳናዊያን ወደ ጎዳናዎች በመውጣት መንገዶችን እንዲያጥለቀልቁ ጠይቀዋል፡፡ሱዳናዊያን አሁን ባለው የፖለቲካ ሂደት ለሁለት የተከፈሉ ሲሆን ለወታደራዊ አመራሩ ድጋፍ የሚሰጥ ባሳለፍነው ቅዳሜ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸው ይታወሳል፡፡
የዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ አሜሪካ የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክር ቤት ስልጣኑን በሲቪል አስተዳድር ለሚመራ መንግስት ካልተሰጠ ድጋፏን እንደምታቆም ከተናገረች በኋላ ነው፡፡
በጀነራል አልቡርሃን የሚመራው የሱዳን ወታደራዊ አመራር ስልጣን ካላስረከበ አሜሪካ ለሱዳን የብድር እፎይታን ጨምሮ ሌሎች ድጋፎችን እንደምታቋርጥ አስታውቃለች፡፡