የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ማንኩራኩር ማርስ ስትደርስ የሀገሪቱ መሪዎች በቀጥታ ስርጭት ተከታትለዋል
በአረቡ ዓለም የመጀመሪያ የሆቸውና “ፕሮብ ኦቭ ሆፕ” የተሰኘ ሥያሜ የተሰጣት መንኮራኩር ወደ ማርስ ምህዋር ገብታለች፡፡ የዩኤኢ እና የመላው አረብ ሀገራት ነዋሪዎች የመንኮራኩሯን በስኬት ማረፍ በጉጉትሲጠብቁ የነበረ ሲሆን አሁን መንኮታኩሯ በስኬት መድረሷ ተነግሯል፡፡
መንኮራኩሯ ማርስ ስትደርስ የሀገሪቱ መሪዎች በዱባይ በሚገኘው የጠፈር ምርምር ማዕከል ሆነው በቀጥታ ተከታትለዋል፡፡
የአቡዳቢ ልዑል አልጋወራሽ እና የዩኤኢ ጦር ኃይሎች ምክትል አዛዥ ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ለጉዞው ስኬት አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን ሁሉ ያመሰገኑት ሼኩ በስኬቱ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡
ስኬታማው ይህ የምንኮራኩሯ ተልዕኮ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችን ከአሜሪካ ፣ ከቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት ፣ ከአውሮፓ ህዋ ኤጄንሲ እና ከሕንድ ቀጥሎ ከዓለም አምስተኛ ሀገር አድርጓታል፡፡
“ፕሮብ ኦቭ ሆፕ” የተሰኘችው መንኮራኩር ዛሬ የካቲት 02 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ ነው ማርስ የደረሰችው፡፡ ፕሮብ ኦፍ ሆፕ ቀይ ቀለም ያላት ማርስ ፕላኔት ላይ ያረፈች ሲሆን መረጃን የመሰብሰብ ተልዕኮ ይኖራታል፡፡