ዩኤኢ በፌዴሬሽን የተዋሃደችበት 49ኛ ዓመት በአዲስ አበባ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ተከበረ
ዩኤኢ እ.ኤ.አ በ1971 በሰባት የተለያዩ ግዛቶች ውህደት ፌዴራላዊ የአስተዳደር ስርዓት ኖሯት መመስረቷ የሚታወስ ነው
በአከባበር ስነ ስርዓቱ የችግኝ ተከላ እና ሌሎችም መርሃ ግብሮች ተከናውነዋል
ዩኤኢ በፌዴሬሽን የተዋሃደችበት 49ኛ ዓመት በአዲስ አበባ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ተከበረ
ዩኤኢ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በሚል በፌዴሬሽን ተዋህዳ የተመሰረተችበት 49ኛ ዓመት በአዲስ አበባ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ተከበረ፡፡
ስነ ስርዓቱ እ.ኤ.አ በ1971 ሰባት የተለያዩ ግዛቶች በፌዴሬሽን ተዋህደው የአሁኗን የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (ዩኤኢ) የመሰረቱበትን ዓመት በማሰብ የተካሄደ ነው፡፡
በስነ ስርዓቱ ችግኝ ተከላን፣ የተማሪዎች ጥያቄ እና መልስን ጨምሮ የሩጫ እና ሌሎችም ስፖርታዊ ውድድሮች ተካሂደዋል፡፡
ይህ የተካሄደው ዩኤኢ በአዲስ አበባ አያት አካባቢ ባስገነባችው ጋራ ጉሪ ትምህርት ቤት ነው፡፡
በስነ ስርዓቱ የተገኙት በአዲስ አበባ የዩኤኢ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ሚዲያ ጉዳይች ኃላፊ ታላል አዚዚ አቡዳቢ ለወጣቶች ከፍተኛ ትኩረት እንደምትሰጥ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያና ዩኤኢ በጋራ ከሚሰሯቸው በርካታ ሥራዎች መካከል አንዱ ወጣቶችን ማብቃት ነው፡፡
ለዚህም ሁለቱ ሀገራት ለወጣቶች ስራ ፈጠራ የሚሆን 100 ሚሊዮን ዶላር ሥምምነት ማድረጋቸው ተጠቅሷል፡፡
በኢትዮጵያ የዩኤኢ አምባሳደር መሐመድ ሳሊም አልራሽድ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ማቲያስ ጋር ተገናኝተው መምከራቸው የሚታወስ ነው፡፡
ቤተክርስቲያኒቷ በአቡዳቢ የራሷ ደብር እንዲኖራት ከአሁን ቀደም መፈቀዱም አይዘነጋም፡፡