ልዩልዩ
ወረርሽኙ ይበልጥ እያደገ ነው የተባለባቸው 11 የአውሮፓ ሃገራት የትኞቹ ናቸው?
በአህጉሩ 30 ሃገራት ያለው የስርጭት መጠንም ባለፉት ሁለት ሳምንታት ጭማሬ አሳይቷል
አብዛኞቹ በምስራቃዊ የአህጉሪቱ ክፍል ይገኛሉ
ወረርሽኙ ይበልጥ እያደገ ነው የተባለባቸው 11 የአውሮፓ ሃገራት የትኞቹ ናቸው?
የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ወረርሽኝ ስርጭት ይበልጥ እያደገ የመጣባቸውን 11 የአውሮፓ ሃገራት ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡
ሃገራቱ ስርጭቱን ለመግታት በሚል ጥለዋቸው የነበሩ እገዳዎችን በማንሳት ላይ መሆናቸውን ተከትሎ ወረርሽኙ ይበልጥ እንዳይስፋፋም ተሰግቷል፡፡
ቢያንስ በአህጉሩ 30 ሃገራት ያለው የስርጭት መጠን ባለፉት ሁለት ሳምንታት ይላል የድርጅቱ የአውሮፓ ማተባበሪያ፡፡
እንደ ማስተባበሪያው ዳይሬክተር ሃንስ ክሉዥ ከሆነ “በተለይ በ11 ሃገራት ወይም አካባቢዎች ዳግም እያገረሸ ያለው የተጠቂዎች ቁጥር በወቅቱ ተገቢውን ምላሽ ካላገኘ የአህጉሪቱ የጤና ስርዓት ዳግም ችግር ላይ ሊወድቅ” ይችላል፡፡
ከ11ዱ ሃገራት አብዛኞቹ በምስራቃዊ የአህጉሪቱ ክፍል ወይም በማዕከላዊ ኤሽያ ይገኛሉ እንደ ዩሮ ኒውስ ዘገባ፡፡
ሃገራቱም ስዊድን፣አርሜንያ፣ሞልዶቫ፣ሰሜናዊ መቄዶንያ፣አዘርባጃን፣ካዛኪስታን፣አልባኒያ፣ቦስኒያና ሄርዞጎቪኒያ፣ኪርዚጊስታን፣ዩክሬን እና ኮሶቮ ናቸው፡፡