በጉባኤው የዩክሬን ቀውስ እንዲሁም መካከለኛው ምስራቅ ቀውሶች በዋናነት ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል
31ኛው የአረብ አገራት የመሪዎች ጉባኤ በአልጄሪያ ተጀመረ
በጉባኤው የዩክሬን ቀውስ፣ የፍልስጤም ጉዳይ፣ ሽብርተኝነት እንዲሁም መካከለኛው ምስራቅ ቀውሶች በዋናነት ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አል ሲሲ፣ የኩዌት ልዑል አልጋ ወራሽ ሼክ መሻል አል አህመድ አል ጃብር አል ሳባህ እና የኳታሩ አሚር ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ ጉባኤውን ለመታም አልጀርስ ገብተዋል።
አያሌ ጉዳዮች ይነሱበታል የተባለው 31ኛው የአረብ አገራት የመሪዎች ጉባኤ የዩክሬን ቀውስ፣ የፍልስጤም ጉዳይ፣ ሽብርተኝነት በመካከለኛው ምስራቅ ያስከተላቸው መዘዞች፣ የሶሪያ፣ የመን እና የሊቢያ ቀውሶች በአጀንዳነት ይነሳሉ ተብሏል።
ከዚህም በተጨማሪም የአየር ንብረት ቀውስ እና “የቱርክና የኢራን ጣልቃገብነት” በአረቡ አለም ዋነኛ የመነጋገሪያ ጉዳይ ከሚሆኑ አርዕስች መሀል ናቸው ተብሏል።
የአልጄሪያው ጉባኤ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት በተለይም በአለም አቀፍ እና በአህጉራዊ ደረጃ ካሉት በርካታ ችግሮች አንፃር በእህት የአረብ አገራት መካከል ለመመካከር እና ለመተባበር ያለመ ነው።
የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ፣ የኩዌት ልዑል አልጋ ወራሽ ሼክ መሻል አል አህመድ አል-ጃብር አል ሳባህ እና የኳታሩ አሚር ታሚም ቢን ሃማድ አል - ታኒን ያካተተው የአረብ መሪዎች ልኡካን አልጄሪያ ዋና ከተማ ሲደርስ ፕሬዚዳንት አብደል-መጂድ ታቡን በአቀባበል አድርገውላቸዋል።
ጉባኤውን አልጄሪያ በሰብሳቢነትም እየመራች ነው።