አረብ ኤምሬትስ ከሩሲያ ጋር ያላትን ትብብር በቀጣይ ዓመታት በእጥፍ አሳድጋለሁ አለች
የአረብ ኤሚሬትስ ፕሬዝዳት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ተወያዩ
ፕሬዝዳት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ የዩክሬን ቀውስ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲቋጭ ጠይቀዋል
አረብ ኤምሬትስ ከሩሲያ ጋር ያላትን ትብብር በቀጣይ ዓመታት በእጥፍ እንደምታሳድግ ፕሬዝዳት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን አስታወቁ።
በሩሲያ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ከሩሲያው አቻቸው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
በዚህም ፕሬዝዳት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አረብ ኤምሬትስ በቀጣይ ዓመታት ከሩሲያ ጋር ያላትን ትብብር በእጥፍ እንደምታሳድግ አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ “ከኮሮና ወረርሽኝ በኋላ ከሩሲያ ጋር ያለን የንግድ ለውውጥ ከ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ወደ 5 ቢሊየን ዶላር በአጥፍ አድጓል” ብለዋል።
ሩሲያ በቱሪዝም ዘርፍ ለአረብ ኤምሬትስ ላደረገችው ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ፕሬዝዳት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ፤ በአሁኑ ወቅት ከ4000 በላይ የሩሲያ ኩብንያዎች በአረብ ኢሚሬትስ ውስጥ እንዳሉ ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅትም በአረብ ኤምሬትስ ውስጥ የሩሲያ ትምህርት ቤት መከፈቱን እና ለዚህም ደስታ እንደሚሰማቸው አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አከለውም የዩክሬን ቀውስ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲቋጭ የጠየቁ ሲሆን፤ አረብ ኤምሬትስ በአለም ላይ የሰላም እና መረጋጋት መሰረትን ለማጠናከር የበኩሏን ጥረት እንድታደርግ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ እየታዩ ላሉ ቀውሶች ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄዎችን ለማግኘት ሀገራው እንደመትሰራም ፕሬዝዳነቱ አረጋግጠዋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በበኩላቸው በገልፍ ቀጠና “ትልቅ” ሲሉ የጠሯትን አረብ ኤምሬትስ ችግሮችን ሚዛናዊ በሆነ መልኩ እንዲፈቱ ለምታሳየው አቋም አመስግነዋል።
ሩሲያ ከአረብ ኤምሬትስ ጋር እያደረገች ያለው ግንኙነት እያገደ መሆኑን ያስታወቁት ፑቲን፤ይህም ለቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ መረጋጋት ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
ሩሲያ፤ አረብ ኤሚሬትስ በዩክሬን ጉዳይ ላይ ላንጸባረቀቸው ሚዛናው አቋም እንደምታመሰግን የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከወራት በፊት በሞስኮ ጉብኝት ላደረጉት የኢሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ አብደላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን መግለጻቸውም አይዘነጋም፡፡
ሀለቱም ሀገራት በተለያዩ መስኮች ዘርፈ ብዙ ትብብር እንደሚያደርጉ ይተወቃል፡፡
በተለይም አረብ ኤምሬትስ ከዓረቡ ዓለም ያደገች ሀገር እንደመሆኗ ሞስኮ-አቡዳቢ ጋር የምታደርገው ትብብር የጎላ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ በሀገራቱ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ መጠን ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ደርሷል።