የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳት መሃድ ቢን ዛይድ ለጉብኝት ወደ ሩሲያ እንደሚያቀኑ ይጠበቃል
የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን በሰርቢያ ጉብኝት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸወ ተነግሯል።
ፕሬዝዳንት መሃመድ ቢን ዛይድ በሰርቢያ ቤልግሬድ በነበራው ቆይታም ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አሌክሳደረ ቪቹክ ጋር መወያየታቸው ታውቋል።
ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ የሰርቢያ ቡንኝታቸውን ማጠናቀቃቸውን ተከትሎም የሀሪቱ ፕሬዝዳንት አሌክሳደረ ቪቹክ በቤልግሬድ አውሮፕላ ማረፊያ ሽኝት እንዳደረጉላቸው የኢሚሬትስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን በመቀጠልም በሩሲያ ለሚኖራቸው ይፋዊ የስፋ ጉብኝት ወደ ሞስኮ እንደሚያቀኑ ይጠበቃል።
ፕሬዝዳንቱ በጉብኝታቸው ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን በመገናኘት አረብ ኢምሬትስ እና ሩሲያ መካከል ስላለው ያለውን ወዳጅነትና ግንኙነት እንዲሁም በተለያዩ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት እንደሚያደርጉ የኤምሬትስ የዜና አገልግሎት ዘገባ ያመለክታል።
የኤምሬትስ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከሩሲያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ትሰጣለች ብለዋል።
ሀገራቸው “የሩሲያ ፌዴሬሽንን እንደ ስትራቴጂካዊ አጋር እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጓደኛ አድርጋ በማየቷ ኩራት ይሰማታል” ሲሉም አክለዋል ሚኒስትሩ።
ጉብኝቱ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ከዓለም አቀፉ ዲፕሎማሲ መድረክ እየተገለለች ላላቸው ሞስኮ ትልቅ ትርጉም አለው ተብሏል።
ሩሲያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በዩክሬን ጉዳይ ላይ ላንጸባረቀቸው ሚዛናው አቋም እንደምታመሰግን የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከወራት በፊት በሞስኮ ጉብኝት ላደረጉት የኢሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ አብደላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን መግለጻቸውም አይዘነጋም፡፡