በአዲስ አበባ በጎርፍ የተወሰደው ህጻን እስካሁን አለመገኘቱ ተገለፀ
የአዲስ አባባ እሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች ፍለጋ ላይ ናቸው
ህጻኑ ከጠፋ አምስተኛ ቀኑ ነው
በአዲስ አበባ ከተማ አዲሱ ገበያ አካባቢ በሚገኘው ላዘሪስት ት/ ቤት ወንዝ ውስጥ የገባው ማርኮን ይገረም አለመገኘቱን የእሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ ።
የአዲስ አባባ እሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የኮሙኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለአል ዐይን አማርኛ እንዳሉት የኮሚሽኑ ሰራተኞች ፍለጋ ላይ ናቸው።
ህጻኑ ከጠፋ አምስት ቀናት ቢቆጠሩም እስካሁን አለመገኘቱን አቶ ንጋቱ ገልጸዋል። በጎርፍ የተወሰደውን ማርኮን ይገረም አካል ለማግኘት ፍለጋው ቀጥሏል ብለዋል።
ህጻኑ ረቡዕ ዕለት ወንዝ ውስጥ የገባው።
ዘንድሮ ትምህርትን "ሀ" ብሎ ሊጀምር በአዲስ አበባ አዲሱ ገበያ አካባቢ በሚገኘው ላዘሪስት ት/ ቤት የገባው ማርኮን ይገረም ባለፈው ረቡዕ ከት/ ቤት ሲወጣ ከት/ ቤቱ አጥር ውጭ ያለው ትቦ ውስጥ በመግባቱ በትቦ ውስጥ የነበረው የጎርፍ ውሃ ይዞት ሄዷል።
ቤተሰብ ቀብሮ እርም ማውጣት ቢፈልግም የ 4 አመቱ ልጅ አስክሬን ግን እስካሁን አልተገኘም።
በት/ ቤቱ አካባቢ ካሉ ወንዞች ጀምሮ የአፍንጮ በር በቀበና በአቃቂ በአባ ሳሙኤልም ባሉ ወንዞች ጎረቤትና ዘመድ አዝማድ እንዲሁም የእሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች ፍለጋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።