ዝቅተኛ የመንግስት እርከን ላይ የሚገኙ ሰራተኞች በስራው ጣልቃ እየገቡበት መሆኑን ምርጫ ቦርድ ገለፀ
ዝቅተኛ የመንግስት እርከን ሰራተኞች ከምርጫው ጣላቃ ገብነት እንቆጠቡ ምርጫ ቦርድ አሳስቧል
እነዚህ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እካልተቆጠቡ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል
ዝቅተኛ የመንግስት እርከን ላይ የሚገኙ ሰራተኞች ምርጫ ጣቢያ ላይ ያለምንም ከቦርዱ የሚሰጥ የፓርቲ ወኪልነትን የሚያሳይ መታወቂያ በመገኘት በቦርዱ ስራ ጣልቃ በመግባት ላይ እንደሚገኙ ምርጫ ቦርድ ገለፀ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ በ6ኛው አጠቃላይ ምርጫ ሂደት የዝቅተኛ የመንግስት እርከን ሰራተኞች (ወረዳ፣ ቀበሌ…ወዘተ) ጣልቃ መግባታቸውን አስታወቀ።
እነዚሁ የመንግስት ሰራተኞች፣ የምርጫ አስፈጻሚዎችን መረጃ መጠየቅ እና በአንዳንድ ሁኔታዎች የመራጮች መዝገብን ለመጎብኘት እና መረጃዎችን ለመውሰድ ጥረት በማድረግ ጣልቃ መግባታቸውን ቦርዱ ገልጿል።
በዚህም መሰረት ማንኛውም ያልተፈቀደለት ሌላ አካል ምርጫ ጣቢያ ውስጥም ሆነ 200 ሜትር ርቀት ዙሪያ ላይ እንዳይገኝ ሲል አሳስቧል።
ማንኛውም የመንግስት እርከን ሰራተኛ ከቦርዱ የበላይ ሃላፊዎች እውቅና በማግኘት ወይም በልዩ የደህንነት ሁኔታ ካልሆነ በስተቀር ለምርጫ አስፈጻሚች ከምርጫ ጋር የተገናኘ ቁሳቁሶችን እንዲያቀንቀሳቅሱ፣ ትእዛዝ አቅጣጫ እና ጥቆማ እንዳይሰጥም አሳስቧል።
ይህ በተለይ የድምጽ መስጫ ቀን እየተጠጋ በመጣ ጊዜ የምርጫ ሂደቱን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያውከው ከመሆኑም በላይ በምርጫ ህጉም ሆነ በወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ የተቀመጠ ወንጀል መሆኑንም አስታውቋል፡፡ እነዚህ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰበው ቦርዱ ይህ ካልሆነ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል፡፡