የመራጮች ምዝገባ ዘግይቶ በተጀመረባቸው ምርጫ ክልሎች ምዝገባ ተጠናቀቀ
በአራቱ የወለጋ ዞኖች እንዲሁም በአማራ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አንዳንድ ስፍራዎች ምዝገባ ዘግይቶ መጀመሩ ይታወሳል
በነዚህ የምርጫ ክልሎች የመራጮች መዝገብ ለሚቀጥሉት 10 ቀናት ለህዝብ ይፋ ይሆናል ተብሏል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርደ ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የመራጮችን ምዝገባ በአጠቃላይ ያጠናቀቀ ቢሆንም ምዝገባውን ዘግይተው የጀመሩ ምርጫ ክልሎች ምዝገባ ሲከናወን እንደነበር ይታወቃል። በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ዘግይተው የጀመሩ ምርጫ ክልሎች ላይ ያለው የመራጮች ምዝገባ ትናንትና መጠናቀቁን ቦርዱ አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት የመራጮች ምዝገባ ትናንትና ግንቦት 13 ቀን 2013 የተጠናቀቀባቸው ቦታዎች
• በምእራብ ወለጋ ዞን ( ለቤጊ እና ሰኞ ገበያ ምርጫ ክልል ውጨ)
• በምስራቅ ወለጋ ዞን ( ከአያና እና ገሊላ ምርጫ ክልል ውጪ)
• በቄለም ወለጋ ዞን
• በሆሮ ጉድሩ ዞን (ከአሊቦ፣ ጊዳም እና ኮምቦልቻ ምርጫ ክልል ውጪ) የሚገኙት 24 የምርጫ ክልሎች ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ሲከናወን የነበረው ምዝገባ እና በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔር ልዩ ዞን የሚገኙት ዳዋ ጨፌ፣ ጨፋ ሮቢት እና ባቲ ምርጫ ክልሎች በተመሳሳይ ሁኔታ ምዝገባው ተጠናቋል።
በዚህም መሰረት በነዚህ ምርጫ ክልሎች የመራጮች መዝገብ ለሚቀጥሉት 10 ቀናት ማለትም እስከ ግንቦት 23 ቀን 2013 ድረስ ለህዝብ ይፋ የሚሆን ሲሆን የመራጮች መዝገባ ቀን ከተጠናቀቀበት ቀን በኋላ ምንም አይነት ምዝገባ ማካሄድ እብደማይቻልም ተገልጿል።