ግድያው ዞኑ በጊዜያዊነት በፌዴራል መንግስት ስር የሚሆንበት መንገድ እንዲመከርበት የሚጋብዝ መሆኑን ኢሰመኮ ገልጿል
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን ተደጋጋሚ የንጹሃን ጭፍጨፋዎች ተፈጽመዋል፡፡ ጭፍጨፋዎች መፈጸማቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በተለያዩ ጊዜያት አረጋግጧል፡፡ ታኅሣሥ 13 / 2013 ዓ.ም ጠ/ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመተከል ጉብኝት ካደረጉ በሀኋላ በዕለቱ ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ 207 ሰዎች ያለቁበት ሌላ ጭፍጨፋ መፈጸሙን ተከትሎ አዲስ ግብረ ኃይል አቋቁመዋል፡፡ ከዚህ በኋላ የተለያዩ እርምጃዎች ቢወሰዱም አሁንም ንጹኃን እየተገደሉ ነው፡፡ ይህ ድርጊት ዞኑ በጊዜያዊነት በፌዴራል መንግስት ስር የሚሆንበት መንገድ እንዲመከርበት የሚጋብዝ መሆኑን ኢሰመኮ ረቡዕ ጥር 05 ቀን 2013 ዓ.ም ገልጿል፡፡