የፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ
ፕሮፌሰሩ ያኔ ርሃብ ኢትዮጵያን በፈተነበት ጊዜ ባደረጉት ተጋድሎ እና በሌሎች ምሁራዊ አበርክቷቸው ሲዘከሩ ይኖራሉ

በስርዓተ ቀብሩ ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተገኝተዋል
የፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ
የፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ስርዓተ ቀብር በአዲስ አበባ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ቤተሰቦቻቸው፣ወዳጅ ዘመዶቻቸውና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት ተፈጽሟል፡፡
በቀብር ስነ ስርዓቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ሂሩት ካሰው (ዶ/ር)፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታጉን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂነር) እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል፡፡
6 ኪሎ በሚገኘው ልደት አዳራሽ ሽኝት ያደረጉላቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አመራሮች እና ምሁራንም በስነ ስርዓቱ ታድመዋል፡፡
ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ከፍተኛ ምሁራዊ አስተዋጽኦዎችን ያበረከቱት ፕሮፌሰር መስፍን ለሃገራቸው በነበራቸው ቀናዒ አመለካከት ይታወቃሉ፡፡
ርሃብ በ50ዎቹ እና 60ዎቹ ኢትዮጵያን በፈተነበት ጊዜ ባደረጉት ተጋድሎ የሚታወሱም ሲሆን የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔን በማቋቋም ጭምር ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ጭምር ኢትዮጵያውያን አይረሱትም፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባስተማሩባቸው ጊዜያትም ሆነ ከዚያ ወዲህ ባበረከቷቸው ምሁራዊ አስተዋጽኦዎችም ትውልድ ሲያስታውሳቸው ይኖራል፡፡
ፕሮፌሰሩ ባሳለፍነው መስከረም 19 ምሽት ይህችን ዓለም በ91 ዓመታቸው መሰናበታቸው የሚታወስ ነው፡፡