"የህልውና ጉዳይ" የሆነው የስዊዘርላንድ የበረዶ መቅለጥ
ስዊዘርላንድ ለአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ትልቅ ቦታ ትሰጣለች
ባለፈው ዓመት የስዊዘርላንድ የበረዶ ግግር ከስድስት በመቶ በላይ መጠናቸው እንደቀነሰ ሪፖርቶች ጠቁመዋል
ስዊዘርላንድ ለአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ትልቅ ቦታ ትሰጣለች። በሀገሪቱ በተለይም እነዚህ ለውጦች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ትልቅ አደጋን ፈጥረዋል።
ስዊዘርላንድ በአየር ንብረት ለውጥ የምትፈተን ሀገር ስትሆን፤ በከፍተኛ ሙቀት መጨመር ምክንያት በጤና ላይ የሚደርሰው ተጽዕኖ ወይም በአከባቢ ደረጃ ታይቶ በማይታወቅ የበረዶ ግግር መቅለጥ ምክንያት የአልፕስ ተራሮችን አለመረጋጋት ገጥሟቸዋል።
ባለፈው ሰኔ ወር በጎርጎሮሳዊያኑ 2050 ወደ ካርቦንን ሚዛናዊ ለመሸጋገር አዲስ ህግ አጽድቃለች።
ህጉ አሁን ያለውን የስዊዘርላንድን የኃይል አማራጮችን በመጠቀም ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ የሆኑ ሁኔታዎችን ይደግፋል።
- ተመድ የአፍሪካ የበረዶ ግግሮች ሊቀልጡ እንደሚችሉና ሚሊዮኖችን ለድርቅ ሊዳርጉ እንደሚችሉ ገለጸ
- ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀው በካይ ጋዝ መጠን መቼ ወደ ዜሮ ይወርዳል?
ይህም በስዊዘርላንድ ውስጥ ያሉ ሁሉንም ዘርፎች ከእርምጃዎቹ ጋር ያለውን ግንኙነት በመደገፍ የአየር ንብረት ለውጥን ለመጋፈጥ አስተዋጽኦ ያደርጋል።
አዲሱ ህግ የኃይል ደህንነትን ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን በስዊዘርላንድ ተራሮች ላይ የበረዶ ግግር መቅለጥ መላ ይላል።
ህጉ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ተራሮቹ በ2002 እና 2022 መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ ያጡትን አንድ ሦስተኛውን የበረዶ ሽፋን ለመቋቋም የሚረዳ ነው።
ህጉ በቅሪተ አካል ነዳጆች ላይ የተመሰረቱ የማሞቂያ ስርዓቶችን ተስማሚ በሆኑ አማራጮች ለመተካት በ10 ዓመታት ውስጥ ሁለት ቢሊዮን የስዊዝ ፍራንክ የሚያወጣ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባትን ያካትታል።
በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የበረዶ ግግር መቅለጥ እና የበረዶ መጠን መቀነስ ክስተት ለስዊዘርላንድ ብዙ መዘዝ እየደቀነ ነው።
ባለፈው ዓመት የስዊዘርላንድ የበረዶ ግግር ከስድስት በመቶ በላይ መጠናቸው እንደቀነሰ ሪፖርቶች ጠቁመዋል።