ለ70 ዓመታት በሰው ሰራሽ ሳምባ ሲተነፍስ የነበረው ሰው ሕይወቱ አለፈ
ግለሰቡ ከብረት በተሰራ ሰው ሰራሽ መተንፈሻ አማካኝነት ከ1952 ጀምሮ በልዩ እንክብካቤ ኖሯል
ፖል አሌክሳንድር አሜሪካዊ ሲሆን በፖሊዮ ምክንያት ከአንገቱ በታች ያለው አካል መንቀሳቀስ አይችልም
ለ70 ዓመታት በሰው ሰራሽ ሳምባ ሲተነፍስ የነበረው ሰው ሕይወቱ አለፈ፡፡
በቅጽል ስሙ ፖል ፖሊዮ ወይም ፖል አሌክሳንድር በመባል የሚታወቀው አሜሪካዊ በፖሊዮ ቫይረስ መጠቃቱን ተከትሎ ነበር ሙኩ ለሙሉ ህይወቱ የተቀየረው፡፡
በተወለደ በስድስት ዓመቱ በፖሊዮ ቫይረስ የተጠቃው አሌክሳንድር ከ1952 ጀምሮ ከአንገቱ በታች ያሉት የሰውነት ክፍሎቹ መስራት ማቆማቸውን ተከትሎ በቴክሳስ ባለ አንድ ሆስፒታል ውስጥ ህይወቱን ሲመራ ቆይቷል፡፡
ይህ ግለሰብ ከበጎ ፈቃደኞች በሚዋጣለት ገንዘብ በሰው ሰራሽ መተንፈሻ መሳሪያ በህይወት መቆየት የቻለ ሲሆን አዕምሮው መስራቱን ተከትሎ በሕግ የመጀመሪያ ድግሪውን ሲይዝ መጽሃፍም መጻፍ ችሏል፡፡
ይህ ሰው ለ70 ዓመታት ከኖረበት ሰው ሰራሽ ብረት ውስጥ እያለ ህይወቱ ማለፉን ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡
ፖል አሌክሳንደር ከአራት ዓመት በፊት በሰጠው ቃለ መጠይቅ በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሞትን እንደፈራ ተናግሮ ነበር፡፡
የወንድ የዘር ፍሬን ጤናማ ለማድረግ የሚጠቅሙ መንገዶች ምን ምን ናቸው?
ሞትን የፈራበት ምክንያት ደግሞ ኮሮና ቫይረስ በእድሜ የገፉ እና ከመተንፈሻ ህመም ጋር በተያያዘ ህመም ያለባቸውን የበለጠ ይጎዳል የሚለውን ዜና በመስማቱም ነበር፡፡
ብዙዎችን ከህይወቱ ያስተማረው ፖል አሌክሳንደር በርካቶች በሆስፒታል እየተገኙም ሲጎበኙት እና ሲያበረታቱት እንደነበር በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ፖል አሌክሳንደር ዓለም እንዲያውቀው እና በጎ ፈቃደኞች እንዲረዱት ያደረገው ክርስቶፈር ኡልመር እንዳለው "ፖል ሁሌም የሚታወስ ሰው ነበር፣ ታሪክህን ስላጋራሀን እናመሰግናለን" ሲል ገልጿል፡፡