በርካታ ተናጋሪ ያላቸው የአለም ቋንቋዎች የትኞቹ ናቸው?
በአለም አቀፍ ደረጃ ከ7 ሺህ በላይ ቋንቋዎች ቢኖረም የአለም ግማሽ ህዝብ የሚጠቀመው 23ቱን ብቻ ነው
በምድር ላይ በተለያዩ መንገዶች ተጽዕኖ በመፍጠር ቋንቋዎች ከአፍ መፍቻ ቋንቋነት ባለፈ በሁለተኛ ደረጃ መግባብያነት በርካታ ተናጋሪዎችን ማፍራት ችለዋል
ቋንቋ የሰው ልጅን ሁለንታዊ ስልጣኔ እና ተጽዕኖ ፈጣሪነት በመወሰን ከፍተኛ ሚና እንዳላው ይነገርለታል፡፡
በዕለት ከዕለት መስተጋበር ፣ በስራ እና ህይወት የተሳካ ግንኙነትን ለማሳለጥ ቋንቋዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ እነዳላቸው ኢትኖሎጂን ጠቅሶ ስታቲስታ ያወጣው መረጃ ያሳያል
በባህል ፣ በኢኮኖሚ ፣ በፖለቲካ የበላይነት እና በቅኝ ግዛት ከቦታ ቦታ የተስፋፉት ቋንቋዎች በርካታ ተናጋሪዎችን ማፍራት ችለዋል፡፡
እንግሊዘኛ ፣ ፖርቺጊዝ ፣ ፍሬንች ፣ ስፓኒሽ እና ሌሎችም ቋንቋዎች አፋቸውን ከፈቱባቸው ዜጎች ባለፈ በአፍሪካ እና በሌሎች የአለም ክፍሎች በርካታ ተናጋሪዎች አሏቸው፡፡
በዚህ የተነሳም በአለም አቀፍ ደረጃ 7 ሺህ ቋንቋዎች ቢኖሩም የምድር ግማሽ የሚሆነው ህዝብ የሚናገራቸው ቋንቋዎች ብዛት 23 ብቻ እንደሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ 15786110
1.42 ቢሊየን ተናጋሪዎች ያሉት እንግሊዘኛ ቋንቋ በአለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ተናጋሪዎችን በመያዝ ቀዳሚው ነው፡፡
380 ሚሊየን በቋንቋው አፋቸውን የፈቱ ተናጋሪዎች ሲኖሩት 1.077 ሁለተኛ ደረጃ ተናጋሪዎችን አፍርቷል፡፡
በመካከለኛው ዘመን በእንግሊዝ እንደተፈጠረ የሚነገርለት ቋንቋ በአሁኑ ወቅት በ67 ሀገራት ይፋዊ የስራ ቋንቋ በመሆን ያገለግላል፡፡
በአለም ላይ በስፋት ከሚነገሩ ቋንቋዎች መካከል 1.38 ቢሊየን ተናጋሪዎችን በመያዝ በሁለተኛነት የሚገኝው በቻይና እና በሌሎች የእስያ ሀገራት የሚገኝው ማንዳሪን ቋንቋ ነው፡፡
በሶስተኛ ደረጃ የሚገኝው ሂንዲ ሲሆን ቋንቋው በህንድ ከሚገኙ 22 ይፋዊ የስራ ቋንቋዎች መካከል አንዱ ነው የቋንቋ ሀብታም በሆነችው ህንድ እንግሊዘኛን ጨምሮ 121 ቋንቋዎች ይገኛሉ፡፡
ስፓኒሽ ፣ ፍሬንች እና አረቢክ ከአራት እስከ ስድስት ያለውን ደረጃ ሲይዙ በቅኝ ግዛት ተስፋፍተዋል የተባሉት ስፓኒሽ እና ፍሬንች ቋንቋዎች እያንዳንዳቸው በ21 እና በ29 ሀገራት ይነገራሉ፡፡