ሩሲያ ምዕራባዊያንን “እጎዳችዋለሁ” ስትል አስጠነቀቀች
ሩሲያ ለምዕራባውያን ማዕቀብ መጠነ ሰፊ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀቷን አስታውቃለች
የሩሲያ የነዳጅ ምርቷ ላይ እቀባ ከተጣለ የ1 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 300 ዶላር ሊደርስ ይችላል ብላለች
ሩሲያ ምዕራባውያን እና ተባባሪዎችቻው የሆኑ የአውሮፓ እና ሌሎች ሀገራት እየጣሉባት ላለው ማዕቀብ ምለሽ ለመስጠጥ እየተዘጋጀት መሆኑን አስታውቃለች።
በዚህም ሩሲያ ምዕራባውያኑን እና ተባባሪዎቻውን “እጎዳችዋለሁ” ስትል ማስጠንቀቋ ተሰምቷል።
መስኮ በዛሬው እለት እንዳስታወቀችው ምእራባውያን እየጣሉባት ላለው ማዕቀብ መጠነ ሰፊ ምለሽ ለመስጠት እየተዘጋጀች ነው።
ሩሲያ ለምእራበውያን የምትሰጠው ምላሽም “በጣም ፈጣን፣ ውጤታማ እና ወሳኝ የሆኑ ሴክተሮችን የሚጎዳ” መሆኑንም አስታውቃለች።
አር.አይ.ኤ የዜና ኤጀንሲ በሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ትብብር ዳይሬክተር ደሚትሪ መሬቸስኪን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ሩሲያ ለምእራባወያን የምትሰጠው ምለሻ “ፈጣን እና ጠንካራ ነው”።
ምእራባውያንን ጨምሮ የአውሮፓ እና ሌሎችም ሀገራት ሩሲያ በዩክሬን ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ መጀመሯን ተከትሎ የተለየያዩ ማዕቀቦችን እየጣሉ ይገኛሉ።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ትናንት ምሽት በሰጡት መግለጫ የሩሲያ ነዳጅ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ ማገዳቸው ተስመቷል።
የሩሲያ በበኩሏ ቀድም ብላ ባወጣችው መግለጫ፤ የነዳጅ ምርት ላይ የሚጣል ማንኛውም እቀባ በዓለም ገበያ ላይ አደገኛ የሆነ ችግር ሊያስከትል ይችላል ማለቷ ይታወሳል።
የሩሲያ የነዳጅ ምርት ላይ እቀባ ከተጣለ አንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ እስከ 300 የአሜሪካ ዶላር ሊደርስ እንደሚችልም ሩሲያ አስጠንቅቃለች።
እንደ ሩሲያ ገለጻ አውሮፓውያን በዓመት 500 ሚሊየን ቶን ነዳጅ ፍጆታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን፤ ከዚህም ውስጥ 30 በመቶ ወይም 150 ሚሊየን ቶን ነዳጅ ከሩሲያ ነው የሚያገኙት።