የፈረንሳይን ጦር ምዕራብ አፍሪካን ለቆ እንዲወጣ ጥያቄዎች በርትተውበታል
ለሳምንት በቡርኪናዊያን ታግቶ የነበረው የፈረንሳይ ጦር በኒጀርም ተቃውሞ ገጠመው፡፡
ፈረንሳይ በምዕራብ አፍሪካ አገራት እያደገ የመጣውን የጽንፈኛ የሽብር ድርጊት ለማስቆም በሚል ነበር ጦሯን ወደ ሳህል አካባቢ ያስገባችው፡፡
ይሁንና ጦሩ በተለይም በማሊ፣ በቡርኪናፋሶ፣ በኮቲዲቯር፣ በኒጀር እና ሌሎች አገራት ቢሰማራም የአክራሪ የሽብር ቡድኖች ጥቃት እየጨመረ መጥቶ በአገራቱ አለመረጋጋቶች ቀጥለዋል፡፡
ሽብርተኞችን ትደግፋለች ያሉ ቡርኪናውያን የፈረንሳይ የጦር ተሽከርካሪዎችን አገቱ
የፈረንሳይ ጦር ባሳለፍነው ሳምንት ከቡርኪናፋሶዋ ካያ ከተማ ወደ ኒጀር ለማለፍ ሲሞክር እቅዱ በከተማዋ ነዋሪዎች መስተጓጎሉ ይታወሳል፡፡
ነዋሪዎቹ ለአንድ ሳምንት ያህል የፈረንሳይ ጦር እንዳያልፍ መንገድ ዘግተው ቆይተዋል፡፡
ይሁንና ጦሩ ከነተሽከርካሪው ከቡርኪናፋሶ አልፎ ወደ ማሊ ሲገባ ተመሳሳይ ተቃውሞ እንደገጠመው ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል፡፡
በኒጀር የተሞከረ መፈንቅለ መንግስት መክሸፉ ተገለጸ
በዚህ የተቃውሞ ሰልፍ ላይም ሁለት ሰዎች ሲሞቱ 18 ሰዎች እንደቆሰሉ ዘገባው አክሏል፡፡
ኒጀራዊያን የፈረንሳይ ጦር “አገራችንን ለቆ ይውጣ፣ ጦሩ ሽብርተኞችን ይረዳል፣ ያሰለጥናል ያስታጥቃል” ሲሉ መናገራቸው ተገልጿል፡፡
በምዕራብ አፍሪካ አገራት እየተፈጸሙ ያሉ የሽብር ጥቃቶች በመጨመራቸው ምክንያት የተማረሩት የአካባቢው አገራት ዜጎች ፈረንሳይ ጦሯን እንድታስወጣ በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡
ኒጀርን ጨምሮ በምዕራብ አፍሪካ በአክራሪ ጽንፈኞች የሚፈጸሙ የሽብር ጥቃቶች እየጨመሩ ሲሆን ፈረንሳይ ጥቃቶቹን ለማስቆም በሚል ከ3 ሺህ በላይ ጦሯን ወደ አካባቢው አገራት ልካለች፡፡
ይሁንና ጥቃቶቹ እየጨመሩ በመምጣታቸው የተማረሩት የአካባቢው አገራት ዜጎች ፈረንሳይ ጦሯን እንድታስወጣ በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡
ፈረንሳይ በሩዋንዳው ዘር ጭፍጨፋ ‘የጎላ ሚና’ እንደነበራት የሚያመለክት የምርመራ ሪፖርት ይፋ ሆነ
በሽብር ቡድኖች ጥቃት የተማረረችው ማሊ ከጽንፈኛ ሀይሎች ጋር የተጀመረውን ዉጊያ ለመመከት ከሩሲያ ቅጥረኛ ወታደሮች ጋር ንግግር መጀመሩን ተከትሎ ፈረንሳይ መበሳጨቷ እና እቅዱ ተቀባይነት የለውም ብሄራዊ ጥቅሜንም ይጎዳል ማለቷ ይታወሳል፡፡