ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዙ ትንታኔዎቻቸው የሚታወቁት ግብጻዊው ሃኒ ራስላን አረፉ
ራስላን በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው ዛሬ ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል
ዶ/ር ሀኒ ራስላን የአል አህራም የፖለቲካ እና ስትራቴጂክ ጥናት ማዕከል አማካሪ ነበሩ
የአፍሪካ ጉዳዮችን በመተንተን የሚታወቁት ግብጻዊው ሃኒ ራስላን (ዶ/ር) አረፉ፡፡
የአፍሪካ ጉዳዮችን በተለይም ከናይል ውሃ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በመተንተን የሚታወቁት ዶክተር ሀኒ ራስላን ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል፡፡
ዶ/ር ሀኒ ህይወታቸው ያለፈው በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው መሆኑን የአል አህራም የፖለቲካ እና ስትራቴጂክ ጥናት ማዕከል የስራ ባልደረባቸው የሆኑት አማኒ ተወከል (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር አማኒ በፌስቡክ ገጻቸው “የሱዳን እና የአፍሪካ ጉዳዮችን ለዓለም እና ለግብጻዊያን በመተንተን የሚታወቁት ዶ/ር ሀኒ ራስላንን ኮሮና ቫይረስ ነጥቆናል“ ብለዋል፡፡
ራስላህ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ በግብጽ ዲፕሎማሲ እና በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ትንታኔዎችን በማድረግ ይታወቃሉ፡፡