ከግብጽ ፒራሚድ እና ከዋሽንግተን ሃውልት የሚገዝፉ አስቴሮይዶች በቀጣዮቹ ተከታታይ ቀናት ምድርን ያልፋሉ ተባለ
‘2021 SM3’ የሚል ስም የተሰጠው ቀዳሚው አስቴሮይድ ነገ አርብ በፈረንጆቹ ጥቅምት 15 እንደሚያልፍ ይጠበቃል
ሆኖም አስቴሮይዶቹ ምድር ላይ እንደማያርፉ እና ይልቁንም ‘በቅርብ ርቀት’ እንደሚያልፏት ናሳ አስታውቋል
ከግብጽ የጊዛ ፒራሚዶች እና አሜሪካ ዋሽንግተን ከሚገኘው ሃውልት የሚስተካከል መጠን ያላቸው ብዙ አስቴሮይዶች ወደ ምድር እየተምዘገዘጉ ነው ሲል የአሜሪካ ብሔራዊ የኤሮኖቲክስ እና ህዋ አስተዳደር (ናሳ) አስታወቀ፡፡
ናሳ አስቴሮይዶቹ እያንዳንዳቸው 160 ሜትር ገደማ ዲያሜትር አላቸው ብሏል፡፡
ትልቁ የጊዛ ፒራሚድ 130 ሜትር፤ የዋሽንግተን ሃውልት ደግሞ 169.29 ሜትር ይረዝማል፡፡
የአፖሎ 11 አብራሪ የነበረው ጠፈርተኛው ማይክል ኮሊንስ በ90 ዓመቱ አረፈ
ወደ መሬት በመምዘግዘግ ላይ ካሉት አስቴሮይዶች መካከል ነው የተባለለት የመጀመሪያው አስቴሮይድ ነገ አርብ በፈረንጆቹ ጥቅምት 15 መሬትን እንደሚያልፍ ይጠበቃል፡፡
አስቴሮይዱ ‘2021 SM3’ የሚል ስም የተሰጠው ሲሆን ከ72 እስከ 160 ሜትር ይረዝማል እንደ ናሳ ገለጻ፡፡
አስተሮይዶቹ መሬት ላይ ያርፋሉ ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ሆኖም በ4.8 ሚሊዮን ኪሎ ሜትሮች ርቀት መሬትን ስተው ያልፋሉ፡፡
ይህ ጨረቃ ከመሬት ካላት ርቀት የሚበልጥ ነው፡፡ ጨረቃ ከመሬት 384,400 ኪሎ ሜትሮችን ትርቃለች፡፡ ሆኖም ናሳ እንዲህ ዐይነቱን ሩቅ ብሎ አይጠራውም፡፡ ይልቁንም ለምድር የቀረቡ (NEO) በሚል ነው የሚገልጻቸው፡፡
‘2021 SM3’ ወደ መሬት ከመጣ ከ5 ቀናት በኋላ ጥቅምት 20 ሌላ ‘1996 VB3’ የተሰኘ ግዙፍ አስቴሮይድ መሬትን ያልፋል፡፡
ከ100 እስከ 230 ሜትር የሚገዝፈው ‘1996 VB3’ በቁመቱ ከካሊፎርኒያው ወርቃማ ድልድይ ይረዝማል፡፡ ይህ ከቀዳሚው የበለጠ መሬትን ቀርቦ እንደሚያልፍ ነው የተነገረው፡፡
‘1996 VB3’ ካለፈ ከ5 ቀናት በኋላ ጥቅምት 25 ደግሞ ከ90 እስከ 200 ዲያሜትር ያለውና ‘2017 SJ20’ የተሰኘ ግዙፍ አስቴሮይድ መሬትን ሳይነካ እንደሚልፍ ይጠበቃል፡፡
ይህ ከግዙፉ የነጻነት ሃውልት በእጥፍ የሚበልጥ ግዝፈት እንደሚኖረው ነው ናሳ ያስታወቀው፡፡
ቁጥር አንዱ የዓለማችን ቱጃር ወደ ጠፈር ሊጓዝ ነው
አስቴሮይዶች በጸሃይ ስርዓት ውስጥ የሚገኙ አነስተኛ ፕላኔቶች ናቸው፡፡