አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሮቦቶች ታካሚን በመንከባከብ ሂደት ውስጥ ጠቃሚ መሆናቸው ተረጋግጧል
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሮቦቶች ሰዎችን ወደ ማከሙ ስራ ሊገቡ እንደሆነ ተነግሯል።
ሮቦቶች በተለይም የታካሚዎችን ጥያቄዎች በማስተናገድ እና ቀላል ተግባራትን በማከናወን በነርሶች ላይ ያሉ ጫናዎችን በቅርቡ ሊወያቀሉ ይችላሉ ነው የተባለው።
በፓሪስ ሆስፒታል በተደረገ ሙከራው፤ አንድሮይድ ሮቦቶቹ ዶከተሮች ሌሎች ስራዎቻውን እንስኪያጠናቅቁ ድረስ ከታካሚዎች ለሚነሱ ጥያቄዎች ምለሽ የሚሰጡ ናቸው።
ሮቦቶቹ ከታካሚዎች ጋር መነጋገርን ጨምሮ፤ ይያቄዎችን መጠየቅ እና መልሶችን መስጠት እንዲሁም የአተነፋፋስ ልምምዶችን እንዲያደርጉም ይረዳሉ ተብሏል።
ሀኪሞቹ ሮቦቶች በርከት ያሉ ታካሚዎች እና ነርሶች በአንድ ጊዜ የሚያደርጉትን ንግግር መስማት መቻላቸውም መሳኝ እንደሚያደርጋቸው ነው የተነገረው።
በፓሪስ በሚገኝ ሆስፒታል ከአረጋውያን ታካሚዎች ጋር የተደረገ ሙከራ ሮቦቶቹ 'ታካሚዎችን መርዳት፣ ጭንቀታቸውን ማቃለል እና በነርሲንግ ሰራተኞች ላይ ያለውን ጫና ማቃለል እንደቻሉ መረጋገጡም ተነግሯል።
ተመራማሪዎች ሮቦቶቹ ብሄራዊ ጤና እንክብካቤን ጨምሮ በጤና አጠባበቅ ውስጥ 'ቀላል ግን ተደጋጋሚ ተግባራትን' በመከወን ወሳኝ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
እንዲሁም በህክምና ባለሙያዎች እና በታካሚዎች መካከል ሊኖር የሚችለውን አካላዊ ንክኪ በመቀነስ የኢንፌክሽን ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ስርጭት ስጋትን እንደሚቀንስ ገልጸዋል።