
በዓሉ ለ 4 ተከታታይ ቀናት የሚከበር ሲሆን እያንዳንዱ ቀን የየራሱ ክብረ በዓል አለው
የተለያዩ እምነቶች በሚንጸባረቁባት ሕንድ በዛሬው ዕለት ‘ፖንጋል’ የተሰኘ በዓል ይከበራል፡፡ ለአራት ተከታታይ ቀናት በደቡብ ሕንድ ፣ በተለይ ታሚል ናዱ ግዛት ፣ የሚከበረው በዓሉ ተፈጥሮ በተለይም የፀሐይ አምላክ የሚመሰገንበት ነው፡፡
የበዓሉ አክባሪዎች ከምስጋና በተጨማሪ በአዲሱ ዓመት የተሻለ ምርት እንዲያገኙ ጸሎትም ለአማልክቶቻቸው ያደርሳሉ፡፡ በምርት ስብሰባ ወቅት የሚከበረው በዓሉ ከ 2,000 ዓመታት በላይ እድሜ እንዳለው ይገለጻል፡፡ ለበዓሉ በሩዝ እና ሌሎች ግብዓቶች ፖንጋል የተሰኘ ባሕላዊ ምግብ ይዘጋጃል፡፡