የኦማን ሱልጣን ሃይታም ቢን ታሪቅ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አረብ ኢምሬትስ ገቡ
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ለኦማን ሱልጣን አቀባበል አድርገዋል
የኦማን ሱልጣን ሃይታም ቢን ታሪቅ በጉብኝታቸው በጋራ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ
የኦማን ሱልጣን ሃይታም ቢን ታሪቅ በአረብ ኢምሬትስ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አቡዳቢ ገብተዋል።
ሱልጣን ሃይታም ቢን ታሪቅ አቡ ዳቢ ሲደርሱም የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ደማው አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የኦማን ሱልጣን ሃይታም ቢን ታሪቅ በአቡ ዳቢ ቆይታቸው ከአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
መሪዎች በአረብ ኢምሬትስ እና ኦማን ታሪካዊ የወንድማማችነት ግንኙነት እና የትብብር መንገዶች እንዲሁም የሁለቱን ሀገራት የጋራ ጥቅም ለማስጠበቅ እና የህዝቦቻቸውን ፍላጎት ማሳካት የሚያስችሉ መስኮች ላይ በጋራ ለመስራም ይመክራሉ።
እንዲሁም በሁለቱ ሀገራ የጋራ ጥቅም አንጻር በቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩም ይጠበቃል።
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ከዚህ ቀደም በፈረንጆቹ 2022 ላይ በኦማን ጉብንት ማድረጋቸው አይዘነጋም።
በዚሁ ወቅትም የኦማን ሱልጣኔት እና አረብ ኢሚሬትስ 16 ስምምነቶችን እና የመግባቢያ ሰነዶችን በተለያዩ መስኮች በተለይም በኢነርጂ እና በኢንዱስትሪ ተፈራርመዋል።
በኦማን ዋና ከተማ ሙስካት በአል አላም ቤተ መንግስት የተፈረሙት ስምምነቶችም የትራንስፖርት፣ የመገናኛ እና የሎጂስቲክስ መስኮች፣ የባህር ትራንስፖርት ዘርፍ እና በኢንዱስትሪ መስኮች ትብብር እና ኢንቨስትመንትን ያካትታሉ መባሉም ይታወሳል።
በተጨማሪም ኦማን ለአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የሀገሪቱን ከፍተኛ ኒሻን ማበርከትዋ ይታወሳል።
ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እንዲጠናከር ላበረከቱት አስተዋጽኦ ነው "አል ሰኢድ" የተባለውን የኦማን ከፍተኛ የኒሻን ሽልማት የተበረከተላቸው።