የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እንደ ሀገር የተመሰረተችበትን 51ኛ ዓመት እያከበረች ነው
51ኛው “የአንድነት ቀን” በተለያዩ መርሀ-ግብሮችና እና ይፋዊ ትርኢቶች እንደሚከበር አዘጋጆች ተናግረዋል።
ኤምሬትስ የምስረታ በዓሏን የምታከብረው ታሪኳን በማጉላትና የወደፊት ምኞቷን በማሳየት ነው።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች 51ኛውን “የአንድነት ቀን” በምስረታዋ የተመዘገቡ አስደናቂ ስኬቶችና ድሎችን በማሰብ በኩራት እና በክብር አከብራለሁ ብላለች።
ኤምሬቶች 51ኛ አመት የአንድነት በዓል ምክንያት በማድረግ መንግስት ታላላቅ መርሀ-ግብር እና ትርኢቶችን አዘጋጅቷል።
የምስረታ በዓል አዘጋጅ ኮሚቴን ጠቅሶ የኤምሬትስ የዜና አገልግሎት እንደዘገበው የአንድነት ቀንን ታላቅ አከባበር በዝርዝር አውጥቷል።
በዚህም መሰረት ዋናው የበዓል አከባበር ነገ ታህሳስ ሁለት እና በተከታዮቹ ቀናት ከታህሳስ ሦስት እስከ ታህሳስ 11 በአቡ ዳቢ ብሄራዊ ማዕከል በተለያዩ ትርኢቶች ለማክበር ታቅዷል።
ከአዘጋጅ ባለስልጣናት አንዱ የሆኑት ሮዛ አል ኩባይሲ እንዳሉት የአንድነት ቀን አጠቃላይ ሀሳብ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ባህላዊ እና ጥንታዊ ቅርሶች እንዲሁም የወደፊት ምኞቶች ላይ የተመሰረተ ነው።
ትርኢቶቹ ለወደፊቱ ብሩህ እና ተስፋ ሰጪ ራዕይን የሰነቁ ናቸው የተባለ ሲሆን፤ በስነ-ስርዓቱ አንድ ሽህ ተማሪዎች ይሳተፉበታል ተብሏል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በየዓመቱ በታህሳስ ሁለት (በፈረንጆቹ) ብሄራዊ ቀኗ አድርጋ ታከብራለች።
እ.አ.አ ታህሳስ ሁለት ቀን 1971 የአቡዳቢ፣ የዱባይ፣ የአጅማን፣ የአል-ዓይን፣ የሻርጃያ እና የኡሙ አል-ኩዋይን ገዥዎች እንደ አንድ ሀገር ለመዋሃድ መስማማታቸውን ተከትሎ ቀኑ የምስረታ ቀን በመባል ይታወቃል።
በሀገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ሼክ ዛይድ ቢን ሱልጣን አል ናህያን መሪነት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እንድትመሰረት ሆኗል። በኋላም እ.አ.አ 1972 ራስ አል ካይማህ ሰባተኛው ኤምሬቶች ለመሆን ወስነዋል። ከዚህን ጊዜ ጀምሮ በየዓመቱ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ብሄራዊ ቀን በመላው የባህረ ሰላጤው ሀገር ይከበራል።