ኤሚሬትስ ሀገር ሆና የተመሰረተችበትን 51ኛ ብሄራዊ በዓል ከሶስት ቀናት በኋላ ታከብራለች።
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ለ1 ሺህ 530 እስረኞች ምህረት አደረገች።
የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ናቸው እስረኞቹ በምህረት እንዲለቀቁ ያዘዙት።
እስረኞቹ በተለያዩ ወንጀሎች ጥፋተኛ ተብለው በማረሚያ ቤቶች የቆዩ ናቸው።
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ 51ኛ ብሄራዊ በዓሏን ከሶስት ቀናት በኋላ ታከብራለች።
ፕሬዚዳንት መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያንም በዓሉን አስመልክተው ነው ለ1 ሺህ 530 እስረኞች ምህረት እንዲደረግላቸው የወሰኑት።
ፕሬዚዳንቱ የሚለቅቁት እስረኞች የሚጣልባቸውን የገንዘብ ቅጣት ለመሸፈንም ቃል ገብተዋል።
የምህረት ውሳኔው እስረኞቹ ቀጣይ ህይወታቸውን የተቃና ለማድረግ ቆም ብለው እንዲያስቡና ቤተሰብ እና ማህበረሰባቸውን በቅንነት እንዲያገለግሉም እድል ይፈጥራል ተብሎ ታምኖብታል ሲል የሀገሪቱ የዜና ወኪል ዋም ዘግቧል።