አሜሪካ ከ450 ሺህ በላይ ዶዝ የኮሮና ቫይረስ ከትባት ለኢትዮጵያ ለገሰች
አሜሪካ ለኢትዮጵያ የሰጠችው የክትባት አይነት ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተሰኘው ነው
የክትባቱን ርክክብ በነገው እለት የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰና የአሜሪካ አምባሳደር በተገኙበት ይካሄዳል
አሜሪካ ከ450 ሺህ በላይ ዶዝ የኮሮና ቫይረስ ከትባት ለኢትዮጵያ መለገሷ ተሰምቷል።
ክትባቱ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ህዝብ በስጦታ የሰጠችው መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለአል ዐይን አስታውቋል።
አሜሪካ ለኢትዮጵያ የሰጠችው የክትባት አይነት ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተሰኘውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት መሆኑ ተገልጽል።
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የተሰጣትን ክትባት የፊታችን ሰኞ ሃምሌ 12 ቀን 2013 ዓ.ም ጠዋቱ ላይ ከአዲስ አበባ ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት እንደምትረከብ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ክትባቱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰና የአሜሪካው አምባሳደር በተገኙበት የርክብክብ ፕሮግራሙ ይካሄዳል ተብሏል።
ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ከ2 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ ለሆነኑ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ አድርጋ ከ277 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 262 ሺህ 200 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።
እስከ ትናንት ሀምሌ 8 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ 4 ሺህ 350 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን እንዳጡ የጤና ጥበቃ ዕለታዊ ሪፖርት ያስረዳል።
ኢትዮጵያ ቫይረሱን ለመከላከል እስካሁን ከ2 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ዜጎች የአስተራ ዘኒካ እና ሲኖ ፋርም የኮሮና ቫይረስ ከተባቶችን የሰጠች ሲሆን የፊታችን ሰኞ ደግሞ የአሜሪካውን ጄ ኤንድ ጄ ክትባት ትረከባለች።